2009-06-12 18:22:27

ዓለም አቀፍ የተፈናቃዮችና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት


የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት በሞቃዲሾ በመካሄድ ላይ ያለው የርስ በርስ ግጭት እየተባባሰ ብዙ ህዝብ ለመሞትና ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ መሆኑ በመጥቀስ የሶማሊያ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

ድርገቱ፣ RealAudioMP3 በግጭቱ ሳቢያ 117 ሺህ ሕዝብ መፈናቀሉና ባልፈው ወር ብቻ በብዛት ሰላማዊ ሕዝብ የሚገኙባቸው በጠቅላላ 20 ሺሕ ያገሪቱ ሕዝብ ለሞት መዳረጉ ባወጣው መግለጫ በመጥቀስ፣ በዚህች አገር የሰብአዊው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በማስታወቅ የግጭቱ ተወናያን ሰላማዊው ሕዝብ ላደጋ ከማጋለጥ ይቆጠቡም ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ችግር በዚህ ብቻ ሳይገታ ህዝቡ ለመፈናቀል አደጋ በተጋለጠበትና በሚገኝበት መጠለያ ሠፈሮች ጭምር ለወሲብ አመጽ መጋለጡ የድርጅቱ መገልጫ ይጠቁማል።

በዚህ ከባለፈው ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚህች አገር ያልቃይዳ የቀኝ እጅ ተብሎ የሚነገርለት በእስላማዊ አክራሪያን ታጣቂ ኃይሎችና በአገሪቱ ጊዚያዊ የሽግግር መንግሥት የመከላከያ ኃይል አባላት መካከል የተቀጣጠለው አዲስ መጠነ ሰፊ ጦርነት ሳቢያ የሕዝቡ ሰብአዊው ችግር እጅግ አሰቃቂ እየሆነ መምጣቱ የተባበሩት መንግሥታት የተፈናቃዮችና የስደተኞች የበላይ ድርገት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.