2009-06-12 14:54:04

በዓለ ቅዱስ ቍርባን


የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትናንት ሓሙስ የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ ወይም በዓለ ቅዱስ ቍርባን የሚከበርበት ቀን ነበር። በኢጣልያና በተቀሩት በዛ ያሉ አገራት ይህ በዓለ ቅዱስ ቍርባን የሚከብረው በሚቀጥለው እሁድ ዕለት ነው። ነገር ግን በቫቲካን ውስጥ ይህ በዓል ልክ የሊጡርጊያ ግጻዌ እንደሚያመለክተው በዕለቱ ከብሮና ተስታውሶ ውሎኣል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይህንን ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ እንደሚደረገው፤ ትናንት ምሽት ወደ ሰበካቸው የቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራን ባዚሊካ በመሄድ በልዩ ልዩ ሥርዓታት የደመቀና ያሸበረቀ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል፣ ስለ ቅዱስ ቍርባንም ሰፋ ያለ ይዞታና መልእክት ያለው ስብከት አሰምተዋል። RealAudioMP3
ከቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራን ባዚሊካ አደባባይ የመሩላና ጐዳናን ተከትሎ በሳንታ ማርያ ማጆረ ባዚሊካ አደባባይ የሚደመደመውን የቅዱስ ቍርባን ዑደትም መርተው በቡራኬ ፈጽመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.