2009-06-12 15:17:51

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 12ኛ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ “ከትላንትና በስትያ “ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ለመቆም የታሪክ መሠረታዊ ምክንያት” በሚል ርእስ ሥር በማርሲሊዮ ማተሚያ ቤት የቀረበው መጽሓፍ በይፋ ለንባብ በቀረበበት ዓውደ ጉባኤ ተግኝተው ባሰሙት ንግግር፣ RealAudioMP3

ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የተለያዩ ርዕሶችን የሚዳስሱ ብዛት ያላቸው ዓዋዲ መልእክቶች የደረሱ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቱን የወጠኑ፣ ጸረ ፋሺሽትና ጸረ ናዚ በጠቅላላ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታትን የተቃወሙ ናቸው በማለት እንደገለጡዋቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ያመለክታል።

ማንኛውም ሰው ለመግለጥ የነበረበት ጊዜና ታሪክ ማጤን ይገባል፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ጸረ የፋሺስትና ጸረ የናዚው ሥርዓት እንደነበሩ ጎልቶ እንዳይታይ በወቅቱ የነበረው የሶቪየት ኅብረትና ከዚህች አገር ጋር ህብረት የነበራቸው አገሮች ሴራ መሆኑ የማይታበል የታሪክ ሓቅ ነው። እውነቱ ገሃድ እንዲወጣም ቅድስት መንበር ስለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሚመለከቱ ሰነዶች ጥናት እንዲደረግ ይኸንን ታሪክ የሚመለከተው የቫቲካን ሚስጢራዊ ቤተ መዛግብት ለታሪክ ተማራማሪዎች ክፍት ለማድረግ እቅድ እንዳላትም በዚህ አጋጣሚ አስታውቀዋል።

ይህ በሎሶርቫቶረ ሮማኖ ዋና አስተዳዳሪ ባቀነባበረው የተለያዩ አበይት ጋዜጠኞች ጽሑፍ በማቅረብ የተሳተፉት ውስጥ ኮሬረ ደላ ሰራ ለተሰኘው የኢጣሊያ እለታዊ ጋዜጣ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት ጋዜጠኛ የታሪክ ሊቅ ፓውሎ ሚየሊ “ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት በነበሩበት ዘመን ይሁን ከተገረሰሱም በኋላ የዚህ ዓይነት ሥርዓት በግልጽ የተቃወሙ መሆናቸው አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.