2009-06-10 16:02:03

የጤና ጥበቃ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አዲስ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነዚግሙንት.


የቅድስት መንበር የጤና ጥበቃ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባላት ዓለም አቀፍ የሕሙማን ዕለት በተመለከተ ለመወያየት መሰብሰባቸው የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ ዚግሙንት ዚሞውስኪ አስታውቀዋል።

የምክር ቤቱ አባላት ነፍሰኄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እኤአ1984 የስቃይ ድኅነት የተሰየመ ያሰተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት በተመለከተ እንደ ሚወያዩ እና ውይይቱ በሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ ዚግሙንት ዚሞውስኪ እንደሚመራ ምክር ቤቱ ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለውል። በቅርቡ የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው የተሰየሙት ብፁዕ አቡነ ሲግሙንድ ዚሞውስኪ በፖላንድ የራዶም ጳጳስ የነበሩ እና የቤተክርስትያን ትምህርት ማኅበር ባለ ሙያ በመሆን ለአሥራ ዘጠኝ ዓመታት ያገለገሉ መሆናቸው የሚታወቅ ነው።

ብፁዕ አቡነ ዚግሙንት ዚሞውስኪ በቅድስት መንበር የጤና ጥበቃ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሆነው በመሰየማቸው ደስታ እንደተሰማቸው እና ከባድ ኀላፊነት መሸከም ማለት መሆኑ ጠቅሰው፡ ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ የጤና ጉዳይ ስለሚንከባከብ ትዝ ያለኝ ነፍሰኄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፡ እኔ እናቴን ብዙ አላስታውሳትም ትዝ የሚለኝ ግን ብዙ መሰቃየትዋ ነው ብለው የነገሩኝን አስታውሳለሁኝ ማለታቸው ተነግረዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብዙ መሰቃየታቸው እና ሲሰቃዩ እናታቸውን ያስታውሱ እንደነበረ እረዳለሁኝ እና የሕሙማን ጉዳይ ጳጳሳዊ ምክር ቤቱ ሕሙማን የመንከባከን ችሎታው ከፍ አድርጎ እንዲሰራ እንደሚሹ አስታወዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.