2009-06-10 15:30:22

የቅዱስ ኲሪኖ ሰማዕትነት 700ኛው ዓመት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በአራተኛው ክፍለ ዘመን በክሮአዚያ የሲሻ ሊቀ ጳጳስት የነበሩት ቅዱስ ሰማዕት ኲሪኖ ሰኔ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. 700ኛው ዝክረ ሰማዕትነት ክብረ በዓል ምክንያት ለክርክ ሰበካ መልእክት አስተላልፈው እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ ር.ሊ.ጳ. በዚህ በክሮአዚያ በክርክ ሰበካ ለየት ባለ መልኩ በተከናወነው መንፈሳዊ ክብረ በዓል የቀረበው መሥዋዕተ ቅዳሴ እሳቸውን ወክለው የመሩት በክሮአዚያ የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆሲፕ ቦዛኒክ መሆናቸውም ተገልጠዋል። RealAudioMP3

ቅዱስ ኵይሪኖ በክርስቶስ ያለውን እምነት በመመስከር የጣዖት አምልኮና መሥዋዕት ማቅረብን በመቃወማሙ ምክንያት እ.ኤ.አ. በ 309 ዓ.ም. ባንገቱ አቢይ ድንጋይ ተንጠልጥሎ በሳቫ ወንዝ ተጥሎ ለሞት መዳረጉ የቤተ ክርስትያን የሰማዕታት የታሪክ ማኅደር ይመሰክረዋል።

ይኸንን የጠቀሰው የር.ሊ.ጳ. መልእክት ቀጥሎም ሰማዕት ኵይሪኖ የቅዱስ ጳውሎስ አብነትን በመከተል በተለይ ደግሞ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፉት ሁለተኛይቱ መልእክት ላይ በምዕራፍ 4 እንደሚነበበው “የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን….” መርህ ቃል በማድረግ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና መከራ ተካፋዮች በመሆን የእርሱ ድል ተካፋዮች መሆናችን እንደምንመሰክር የሚያበስረውን የጳውሎሳዊ መንፈስዊነትን በመኖር ሰማዕትነት የተቀበለ ቅዱስ ኵይሪኖ አማላጅነት ለክሮአዚያና ለክርክ ህዝብ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቸው ዘንድ እንደሚጸልዩና ምእመናን ሁሉ የዚህ ጸሎት ተካፋዮች ይሁኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ቦዛኒች ምእመናንን ያበረታቱ ዘንድ ቅዱስ አባታችን አደራ ማላታቸው ተገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቦዛኒች “የቅዱስ ሰማዕት ኵይሪኖ ምስክርነት የዛሬ የክሮአዚያ እምነት መሠረት መሆኑ” ለቅዱስ ሰማዕት ኵይሪኖ ለመዘርከር ያረገው መስዋዕተ ቅዳሴ መረተው ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ “ሕያው የእምነት ሃብት ውርሻ መሆኑና ይኽ ደግሞ ዛሬ የክሮአዚያ ምእመናን እምነታቸው በማኅበራዊ ሕይወት ሕያው ያደርግ ዘንድ ያነቃቃል” ብለዋል። “የእምነት ሰማዕትነትና ስለ እምነት መሰደድ በቀዳሚው ክፍለ ዘመን ለነበረችው ቤተ ክርስትያንና ምእመናን የሚመለከት እንዳልሆነ በኮሙኒዝም ሥርዓት ዘመን የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳሳት የነበሩት እ.ኤ.አ. በ 1960 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ብፁዕ ካሪናል አሎይዚየ ስቴፒናክ በነበረው የጸረ እምነት ሥርዓት ሳይበገሩ በቆራጥነት ወንጌል በመስበክ የመሰከሩት እምነትና የቤተ ክርስትያንን አንድነት አንዱ አብነት ነው” ብለው “እምነት በእሥራት የሚገታ አማኞችን በማሳደድ የሚቀጭ አይደለም፣ ይህ ደግሞ አሳዳጆች ፍጻሜ አለ መሆናቸው ያስረዳናል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ይሚያጠፋ የሚያፍን ኃይል አልነበረም የለምም አይኖርምም ይህ ደግሞ የሰማዕት ታሪክ ሕያው ምስክር ነው” እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.