2009-06-10 14:25:00

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2009)


ቅዱስነታቸው ዛሬ በተለያዩ ቋንቋዎች ያስተማሩትና የገለጡት በንጉሥ ካርልማኝ ዘመን ስለኖረው ዮሓንስ ስኮቱስ ኤሪጂና በመባል ስለሚታወቀው እና ከፍተኛ ተደማጭነት ስለነበረው ከቤተ ክርስትያን አበውና ጸሓፍት አንዱ ነው። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት እንደሚከተለው ነው።
“ኤሪጂና ስለ ምሥራቁ ሃይማኖተ አበውና ትምህርተ አበው ወይም ነገረመለኮት የነበረው ፍቅርና ስሜት በተለይ ስለ ዲዮናስዩስ ኣጥንቶ ፤ ጽሑፎቹን ሁሉ በዝርዝርና በጥንቃቄ ወደ ላቲን ቋንቋ እንዲ ተረጉም ገፋፋው። እንድ ኤሪጂና እምነት ኣማኝ የሆነው ሁሉ በመለኮትነት ባህርዩን የምንሳተፈውን ኣምላክ ተምስጦአዊ ስግደት ወይም ኣምልኮ ማቅረብ እስክሚቻለው ድርስ ሓቅን መፈለግ ወይም መሻት የግድ ይለዋል፤ የሚል ነበር ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ስግደት እና አምልኮ ተመክሮ በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል የኤሪጂና ተዮሎጊ ቀጣይነት የሚያገኘው በአታፋሲስ ማለት ኣስቀድሞ ኣምላክ ያልሆነውን ነገር በማወቅና በማረጋገጥ ነው”።







All the contents on this site are copyrighted ©.