2009-06-10 15:47:41

ብፁዕ ካርዲናል ኦብራያን በአይርላንድ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዩ መልእክተኛ፡


ብፁዕ ካርዲናል ከይት ማይክል ፓትሪክ ኦብራያን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ልዩ መልእክተኛ በመሆን በአይርላንድ በሎንግ ታወር የሚታወቀው የቅዱስ ኮሉምባ ቤተክርስትያን መቶኛ ዓመት ዝክረ በዓል ለመገኘት ትናንትና ወደ ደሪ አይርላንድ መሄዳቸው ቅድስት መንበር ያወጣችው መግለጫ አስረድተዋል።

የቅዱሳን አንድሪው እና ኤዲምበርግ ሊቀጳጳስ በዚሁ የቅዱስ ኮሉምባ ቤተክርስትያን መቶኛ ዓመት ዝክረ በዓል መሳተፋቸውም ተመልክተዋል።

የቅዱስ ኮሉምባ ወይም ሎንግ ታወር ቤተክርስትያን እኤአ በ546 ዓመተ ምሕረት በቅዱሱ በተቈረቈረው ገዳም የምትገኝ ታሪካዊ እና የጠቅላላ አይርላንድ ክርስትያናዊ ቅርስ መሆኑ በሰፊው የሚነገርለት ቤተክርስትያን መሆኑ የሚታወስ ነው

ዛሬ ጥዋት የቅዱስ አባታችን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ልዩ መልእክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ከይት ማይክል ፓትሪክ ኦብራየን በርካታ ጳጳሳት ካህናት መነኲስያት እና መነኮሳት በተገኙበት በቅዱስ ኮሉምባ ቤተክርስትያን መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል ።

በሮማ የአይርላንድ ኮሌጅ ዳይረክተር አባ አልበርት ማክዶናልድ እንዳመለከቱት፡ ቅዱስ ኮሉምባ ሰባኪ ቅዱስ ውንጌል ጥንታውያን ገዳማት የቐረቐረ የንባበ መለኮት ሊቅ ነበር ።

ቅዱስ ኮሉምባ የመሀከለኛው ዘመን ቤተክርስትያን ብርሃንዋ እንድትሰጥ ጥረት ያደረገ በግዜው የነበሩ ግጭቶች በሰላም እንዲወገዱ ያደረገ ዘወትር የጸለየ ፍጡር ሁሉ የወደደ መንፈሳዊ መኖሩ አባ አልበርት ማክዶናልድ ገልጸዋል።

ቅዱስ ኮሉምባ እኤአ 563 ዓመተ ምሕረት ከአራ ሁለት ጓደኞቹ ከደሪ ወደ ስኮትላንድ ያመራ፡ እዚያው ዮና በተባለች ደሴት በ597 ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ጥንታዊ መንፈሳዊ እና ብልህ ቅዱስ መሆኑ የአይርላድ ኮሌጅ ዳይረክተር አባ አልበርት ማክዶናልድ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.