2009-06-09 09:06:22

የእኅው ራፋኤለ ራፊሪንጋ ብፁዕና በማዳጋስካር


የላሳል ማኅበር አባል የማዳጋስካር ተወላጅ እ.ኤ.አ. በ 19ኛውና በ 20 ኛው ዘመን የኖረ ወንድም ራፋኤለ ራፊሪንጋ ትላትና በማዳጋስካር ርዕሰ ከተማ

RealAudioMP3

የቅዱሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ አማታ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፅእና እንደታወጀላቸው ተገለጠ።

ብፁዕ ወንድም ራፊሪንጋ እ.ኤ.አ. በ 1856 ዓ.ም. በማዳጋስካር እንደተወለደና የመጀመሪያ ማዳጋስካራዊ የላሳል ማኅበር አባል ለመሆን የበቃ፣ ከዚህች አገር በጠቅላላ ልኡካነ ወንጌል እንዲወጡ ከተደርጉ በኋላ በሁሉም ያገሪቱ ካቶሊክ ምእመናን የዚህች ደሴት ቤተ ክርስትያን መሪ እንዲሆን ተመርጦ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ትምህርተ ክርስቶስ በማስተማር የተለያዩ መፍነሳዊና ባህላዊ መጽሓፍቶችንም በመድረስ ለቤተ ክርስትያንና ለሕዝበ እግዚአብሔር የሰጠው አገልግሎት የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መሠረት ከሆኑት አበይት ውስጥ እንዲጠቀስ ማድረጉ ዜኒት የዜና አገልግሎት ያስራጨው ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.