2009-06-09 09:15:38

የቅድስት ሓና ቍምስና በቫቲካን የራሱ አዲስ ድረ ገጽ ከፈተ


በቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር የሚተዳደረው የቫቲካን ቁምስና የቅድስት ሃና ቤተ ክርስትያን የራሱ አዲስ ድረ ገጽ መሥራቱ ተገለጠ። RealAudioMP3 ይህ ዳብሊው ዳብሊው ዳብሌው ሳንታና ነጥብ ቪኤይ በሚል አድራሻ የተሠራው ድረ ገጽ ቁምስናው የሚያከናወነው መንፈሳዊ ሰብአዊና ባህላዊ አገልግሎቶችን አቢይ ግምት የሚያሰጠው ሲሆን፣ በቫቲካንና በኢጣሊያ በሚያዋስነው በአገረ ቫቲካን ውስጥ ያለው ቤተ ክርስትያን በቫቲካን ለሚኖሩ የቁምስናው አባላት ብቻ ሳይሆን በቫቲካን መንፈሳዊ ንግደት ለማካሄድ በቁምስናው ለሚገኙት ነጋድያን ጭምር የሚመለከት ድረ ገጽ መሆኑ ቆሞስ አባ ሲልቨስትሪኒ መግለጣቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ትላትና ባወጣው ኅትመቱ አስታወቀዋል።

በዚህ ድረ ገጽ የቁምስናው መርሃ ግብሮችና የሚሰጠው አገልግሎት እንዲሁም የቤተ ክርስትያንዋ ታሪካ ተዘግቦ እንደሚገኝም ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.