2009-06-09 09:28:26

የስዑድ ዓረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ጉብኝት በቫቲካን


RealAudioMP3 የስዑድ ዓረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ልኡል ሳውድ ፋይሳል ቢን ዓብደልዓዚዝ እ.ኤ.አ. ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደውን ውይይት በሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራንና በዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፒየር ልዊጂ ቼላታና ምክትል ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አንድረው ቪዛኑ ዛንያ አናን እና በዚሁ የጳጳሳዊ ምክር ቤት ከእስላም ሃይማኖት ጋር የሚካሄደውን ግኑኝነት ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ክሃለድ አካሼሕ ተሸኝተው በቫቲካን ይፋዊ ጉብኝት በማካሄድ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ ጋር ተገናኝተዋል።

በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት እ.ኤ.አ. ከስኔ 16 ቀን እስከ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በስዑድ ዓረብ ንጉሥ ዓብዱላህ ቢን ዓብደልዓዚዝ አል ሳውድ በሃይማኖቶች መካከል የሰላም መሠረት የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት መሆኑ በማመን በዚህ እቅድ መሠረት በማድሪድ ተካሂዶ ስለ ነበረው ጉባኤ በተመለከተ ሐሳብ ለሐሃሳብ ተለዋውጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.