2009-06-09 09:10:25

ወጣቶች ትምህርትና ቤተ ሰብ


የስካላብሪኒያኒ ማኅበር አነሳሽነት ትላትና በሮማ ከተማ የሚኖሩት የውጭ አገር ዜጎች በተለይ ደግሞ እዚህ ሮማ ከውጭ አገር ዜጎች የተወለዱት ወጣቶች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ RealAudioMP3 ለማድረግ ስደተኞች በጠቅላላ ከተስተናገዱበት አገር ጋር እንዲተዋወቁ፣ብዙ ስደተኞች እያጋጠማቸው ካለው ተገሎ ከመኖር ማኅበራዊና ሰብአዊ ችግር ለማላቀቅ በማቀድ በመሰባሰብ ስለ ስደተኛውና የስደተኛው ሕይወት በጋራ በማስተንተንና ሐሳብ ለሐሳብ ለመለዋወጥ መገናኘታቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ እዚህ ሮማ የሚገኘው ጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ ወጣት፣ የህንጸት መደብና ቤተሰብ በተሰኘው ርዕሥ ያነሳሳው ዓውደ ጥናት መከናወኑ ተገለጠ። ይህ በቤተ ክርስትያንና በትምህርት ያሰጣጥ ሥርዓት ቤተሰብ ማዕከል ይሆን ዘንድ የተገለጠበት ዓውደ ጥናት መሆኑም ሲገለጥ። ይህ ዓውደ ጥናት የነገውን አላውቅም የሚለውን አነጋጋር በሁሉም ዘርፉ እየተገለጠ እያስከተለው ያለው ማኅበራዊ ሰብአዊ መንፈሳዊ ችግት በመተተን የችግሩ መፍትሄ ምን መሆን እንደሚገባውን የተነተነ መሆኑም ለማወቅ ተችለዋል።

በሳል ፍቅር ዘላቂነት ያለው የፍቅር ባህል በማኅበረሰብ ዘንድ እንዲሰርጽ ምን መደርግ እንዳለበት ብቻ ሳይሆን እ.ፈ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ኢስታት የኢጣሊያው የስታቲስቲክስ ማዕከል በኢጣሊያ ተፋቶ ዳግም ትዳር የሚመሠርተው የማኅበረሰብ ክፍል ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱና የመፋታቱ ችግር በሚወለዱት ሕጻናት ላይ የሚያስከትለው ችግር ሁሉ አንድ ባንድ በመገምገም የፍቅር ጥልቅ ሚሥጢር ሁሉም እንዲረዳውና ቤተሰብ በዚሁ ዘርፍ በማነጽ ጤናማ ማኅበረሰብ ለመገንባት የተሰኘው አመለካከት የጐላበት ዓወደ ጥናት እንደነበር ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.