2009-06-05 16:06:20

ደቡብ አፍሪካ


በደቡን አፍሪካ ላርባ ዓመት ያገለገሉት የማሪያንሂል ልኡካን ማኅበር አባል የኦስትርያ ተአላጅ ወንድም ኤርንስት ፕሊዩኽል በማሪያዘል ክልል በሚገኘው ቤታቸው እያሉ በወረበሎች እጅ መገደላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ እዛው ሓዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡበት በነበሩበት ማሪያዘለ ከተማ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ዛሬ መፈጸሙ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

የአባ ፕሊዩኸል ሰማዕትነት ለአገሪቱ ቤተ ክርስትያን ለምትሰጠው አገልግሎት አቢይ መፍነሳዊ ድጋፍ እንደሚያስገኝም አያጠራጥርም። የጆሃንስ በርግ ሰበካ በክልሉ ለሚገኙት የዚምባብዌ ስደተችን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ሲነገረ፣ አዲሱ የደቡብ ኣፍሪካ መንግሥት ከዚህች ጎረቤት አገር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሚሻው የዚምባብዌ ዜጋ በአገሪቱ ከሚገኘው የደቡብ ኣፍሪካ ልኡከ መንግሥት ጽ/ቤት የይለፍ ፈቃድ እንደማያስፈልገው ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ወደ ጆሆንስ በርግ የሚገብው የዚምባቤው ስደተኛ ዜጋ ብዛት እጅግ ከፍ እያለ በመሆኑ የጆሃንስ በርግ ሰበካ ለስደተናው ህዝብ የሚሰጠው አገልግሎት በእጥፍ ከፍ እንዲሉ ማድረጉ ተገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.