2009-06-05 16:02:43

የዛሬ ሃያ ዓመት በቴንአንመን የተደረገ የቻይና ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ


እ.ኤ.አ. ሰኔ 4 ቀን 1989 ዓ.ም. በቻይና በሚገኘው ተነንመን አደባባይ፣ በቻይና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይረጋገጥ ዘንድ ተማሪዎች ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ለማፈን የአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች፣ ኃይል በመጠቀም የወሰዱት እርምጃ ሳቢያ፣ የተለያዩ የሰብአዊ መብት አስከባሪ ማኅበራት በሺ የሚገመቱ ተማሪዎች መገደላቸው ቢናገሩም ቅሉ፣ የአገሪቱ የይፋ መግለጫዎች ግን በተማሪዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ 241 ተማሪዎች ብቻ ሕይወታቸው እንዳጡ የሚነገርለት የዛሬ 20 ዓመት በፊት የተከሰተው በተማሪዎች የተከፈለው መሥዋዕት በተለያዩ አገሮች መዘከሩ ተገለጠ።

ቀኑን ምክንያት በማድረግም አምነስት ኢንተርናሺናል፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር፣ በቻይና የሰብአዊ መብትና ፈቃድ እንዲከበር ጥሪ በማቅረብ በትያናመን አደባባይ በተማሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ የሚያጣራ አንድ ነጻ ያጣሪ ድርገት ይመለመልም ዘንድ ጥያቄ አቅርበዋል። ቀኑ ለተለያዩ ተቃውሞ መገልጫ ሰበብ ሊሆን ይችላል በሚል ሥጋት በቲያናንመን አደባባይ የጸጥታ ኃይሎች በገፍ መሠማራታቸው ለማወቅ ተችለዋል። ስለዚህ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጉዳይ በተመለከተ፣ ጳጳሳዊ ለውጭ የግብረ ተልእኮ ማኅበር አባል በቻይና በሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ያገለገሉ ኣባ አንጄሎ ላዛሮቶ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የዛሬ 20 ዓመት በፊት የቻይና ተማሪዎች ያነሳሱት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጥያቄ መንግሥት ለመገልበጥ ያቀደ ጸረ መንግሥት አድማ አልነበረም። እንዲያውም በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ አገሪቱን የሚመራዊ የፖለቲካ ሰልፍ አባላት ጭምር ነበር የተሳተፉበት፣ ስለዚህ ሰላማዊው ሰልፉ ኢፍትሐዊነት፣ ሙስናን፣ ብቃት አልቦ የመስተዳድር ጉዳዮች የመሳሰሉትን በመቃወም ነበር የተካሄደው። በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ መንግሥት መጠነኛ ለውጥ ያሳየ ቢመስልም ቅሉ፣ ተማሪዎች ያቀረቡት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ መልስ አላገኘም። ያ ተማሪዎች የቀሰቀሱት ማኅበራዊ ኅሊና በተለያዩ አገሮች በስደት የሚኖሩ የቻይና ምኁራን አማካኝነት እየተስተጋባ ነው” ብለዋል።

“ሕዝብ የማፈኑ ፍላጎት አሉታዊ ጉዳዮች ገሃድ እንዳይወጡ መራወጥ ማለት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. 2007 ዓ.ም. ለቻይና ቤተክርስትያን ባስተላለፉት መልእክት፣ ባለፈው ግንቦት የማብራሪያ መልእክት የታከለበት እንደሚያመለክተው፣ የቻይና ምእመናን ከአገሪቱ መንግሥት ከክልል መስተዳድሮች ጋር መከባበር የተካነው ገንቢ ውይይት ያካሂዱ ዘንድ ማሳሰባቸው ለማወቅ ሲቻል። ር.ሊ.ጳ. የቻይና መንግሥት ለካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚጠቅም ውሳኔዎችን ያረጋገጥ ዘንድ ሳይሆን፣ የጋራ መከባበርና መግባባት የተካነው ግኑኝነት ይኖር ዘንድ የሚጠይቅ ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.