2009-06-05 16:05:02

ንኡሳን አኅው ፍራንቸስካውያን ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ


የንኡሳን አኀው ፍራንቸስካውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ ለመምረጥና የማኅበሩ ጉዳይ ለመገምገም 152 የማኅበሩ ተወካዮች የጠራው እስከ ስኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚዘልቀው 187ኛው ጠቅላይ ጉባኤው እያካሄደ ነው። ይህ በአሲዚ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ዘመላእክት እየተካሄደ ያለው ጉባኤ የር.ሊ.ጳ. ልዩ ወኪል ብፁዕ ካርዲናል ኾሰ ሳራይቫ ማርቲነስ በተገኙበት የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ ሆነው ያገለገሉት፣ የኃላፊነቱ ተልእኮአቸው ያጠናቀቁት ኣባ ሮድሪገዝ ካርባሎ ዳግም የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ እንዲሆኑ ጉባኤው መርጧቸዋል።

ኣባ ካርባሎ 56 ዓመት እድሜ ያላቸው የስፐይን ተወላጅ፣ ከተለያዩ አግሮች የተወጣጡ በ 113 አገሮች የሚገኙት በጠቅላላ 15 ሺህ የንኡሳን ፍራንቸስካውያን ማኅበር አባላትን እስከ 2015 ዓ.ም. ጠቅላይ አለቃ በመሆን ይመራሉ። ኣባ ካርቦሎ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስም፣ “የማኅበሩ ዳግም ጠቅላይ አለቃ ሆኜ እንዳገለግል ወንድሞቼ መርጠውኛል፣ ይህ ደግሞ በኔ ላይ ያላቸውን እማኝነት አቢይ መሆኑ ያመለክተኛል። ስለዚህ ይህ ደግሞ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የማኅበሩ እውነተኛ ጠቅላይ አለቃ መንፈስ ቅዱስ እንዲሆን ይገልጠው የነበረው ፍላጎቱ በመከተል ማኅበሩ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ እራሱን ሳይዘጋ ለወቅታዊውና ለመጪው ሁኔታ ክፍት በማድረግ፣ ወቅቱ የሚያመጣውን ፈተና በመሻገር በቤተ ክርስያን ከቤተ ክርስትያን ጋር በመሆን የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር የሚመሰክር ነው” ብለዋል። ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ፣ የአንድ እግዚአብሔር አባትናት በጥልቀት በመረዳት ኩላዊው ወንድማማችነትን በቃልና በሕይወት ያስተማረውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በመከተል እግዚአብሔር ለሁሉም የሰው ዘርና ለተፈጥሮም ጭምር መሆኑ በመገንዘብ የእግዚአብሔርን ውበት ያበስራል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.