2009-06-03 20:21:18

“ዶን ቦስኮ ትላትና እና ዛሬ”


RealAudioMP3 ቅዱስ ዮሓንስ ዶ ቦስኮ የተወለደበትን ሁለት መቶኛው ዓመት ምክንያት ለመዘከር የዚህ ቅዱስ ትርፋት እዚህ ሮማ ከሚገኘው የሳን ካሊስቶ የቀደምት ክርስትያን ሰማዕታትነት በተቀበሉበት ዋሻ ጀምሮ በተለያዩ አገሮች ዑደት እንደሚያደርግ ተገልጠዋል። ባለፈው እሁድ እዚህ ሮማ የሚገኘው በዶን ቦስኮ ማህበር አባላት በሚመራው የቀደምት ክርስትያን ሰማዕታት ትሩፋት በሚገኝበት ዋሻ እንዲያርፍ ተደርጎ ለሁሉም ነጋድያን ምእመናን መቅረቡ ሲነገር፣ እስከ ሚቀጥለው ዓርብ እዛው እንደሚቆይም ተገልጠዋል።

ዶን ቦስኮ የተወለደበት ሁለት መቶኛውን ዓመት ለመዘከርም “ዶን ቦስኮ ትላት እና እና ዛሬ” በሚል ርዕስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ተገልጠዋል። በዚህ ዓውደ ጥናት ጳጳሳዊ የቲዮሎጊያና የሳሊሲያን ሓዋርያዊ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት አባል አባ ኤንሪኮ ዳል ኮቮሎ መሳተፋቸው ተገልጠዋል። አባ ዳል ኮቮሎ በሰጡት አስተምህሮ የሳሊዚያን ማኅበር የተመሠረተበት 150ኛው ዓመት ዘንድሮ እንደሚዘከርም ጠቅሰው፣ ይህ ማኅበር በ 15 ሺሕ 750 የማህበሩ አባላት አማካኝነት በ 129 አገሮች ሓዋርያዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ገልጠዋል።

“ቅዱስ ዶምቦስኮ እምነትንና ምርምርን በማጣመር ለሌሎች ማስተማር የሚለውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አንግቦ በማስተማር፣ በተለይ ደግሞ ለወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ሰብአዊ፣ ባህላዊና መንፈስዊ ህንጸት በማቅረብ እምነትን በመመሥከር፣ ቤተ ክርስትያንና ሕዝበ እግዚአብሔር ያገለገለ፣ በዚህ በርሱ በተቋቋመው ማኅበር አምካኝነትም በቤተክርስትያን ከመንፍስ ቅዱስ የተቀበለው ስጦታ ዛሬም እየቀጠለ ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.