2009-06-03 20:21:01

የካቶሊክ ተግባር እንቅስቃሴ


የኤውሮጳ ኅብረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማደስ ከ ሰኔ 4 ቀን እስከ ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በሁሉም አባል አገሮች ምርጫ እንደሚካሄድ ተገለጠ። ስለዚሁ ህዝባዊ ምርጫ ጉዳይ በማስመልከት የካቶሊክ ተግባር እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ፍራንኮ ሚላኖ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “የኤውሮጳ ባህል መሠረት የሆነውን የክርስትናው ባህል ጎልቶ መታየት ይኖርበታል። ኤውሮጳ ይኸንን መሠረታዊ ባህልዋ ለይታ ዳግም ካልተጎናጸፈች ከሌሎች ባህሎች ጋር ለመገናኘት ያዳግታታል፣ ማለትም እራስህን ጠንቅቀህ ማወቅ ሌላውን ለማወቅ መሠረትና ሚዛን ነው” ብለዋል።

“መጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቀጥለውም ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ኤውሮጳ መለያዋን ለይታ በማወቅ በሮችዋን ክፍት ማድረግ” ያሉትን ሀሳብ በማስታወስ፣ “ስለዚህ ኤውሮጳ ክርስትያናዊ እሰይታዎችን በመኖርና በመግለጥ በቀላሉ ከሌሎች ጋር ለመገናኘትና በሮቿን ክፍት ለማድረግ ትችላለች፣ ክርስትያናዊ እሰይታዎች የምንላቸው በሌላው አገላለጥ የሰብአዊ አንድነት የሚወክሉ ናቸው ብለዋል። ኅብረቱ የህዝብ ተሳታፊነት የሚጎላበት መሆን ይኖርበታል፣ የህዝብ ተሳትፎ የሚንጸባርቀበት ከሆነ ለሕዝብ ቅርብ ይሆናል ስለዚህ ኅብረቱን የሚገነባው ሕዝባዊ ተሳትፎ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.