2009-06-03 20:20:33

የመስተንግዶ ሐዋርያዊ ኖልዎ


RealAudioMP3 በጓተማላ በምትገኘው በተኩም ኡማን ከተማ “ሲኖዳዊት ቤተ ክርስትያንና የመስተንግዶ ሐዋርያዊ ኖልዎ” በተሰኘ ርዕስ ሥር ትላት የተጀመረው የመካከለኛው የላቲን ኣሜሪካ አገሮችና የካሪቢያን እንዲሁም የሰሜን አሜሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ እያሳተፈ ያለው ጉባኤ በንግግር የከፈቱ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ “የቤተክርስትያንን እውነተኛው ስነ አካል ለሚስደደውና ለሚፈናቀለው የሐዋርያዊ ኖልዎ እንክብካቤ በመስጠት ጉልህ ማድረግ ይገባል” እንዳሉ ተገልጠዋል።

ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ “ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የቤተክርስትያን ምስል መግለጫ በሆነው ሰነድ ዘንድ ያለው “ሉመን ጀንዚዩም፦ ብርሃነ አሕዛብ” የተሰኘውን ውሳኔ ዋቢ በማድረግ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ከሕዛብ ጋር የምተወያይበት አዲስ ቋንቋ መሆኑ ገልጠው፣ የዚህ የቤተክርስትያን ሰነድ ተግባራዊ ገጽታውን አብራርተዋል። በመቀጠልም የዛሬ 5 ዓመት በፊት ይህ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኤርጋ ሚግራንተስ ክሪስቲ - የክርስቶስ ፍቅር ለስደተኞች በተሰኘው ርዕስ የተደረሰው የዚህ ሐዋርያዊ ኖልዎ መመሪያ በስፋት አስረድተዋል። ይህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያረቀቀው መመሪያ የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያናት ለስደተኞችና ለተፈናቃዮች በሚሰጡት አገልግሎት መሠረት የቤተ ክርስትያን አንድነትንም ጭምር በተግባር ይመሰክራሉ” ብለዋል።

በቤተ ክርስትያን ሁሉም አለ ምንም አድልዎ እኩል መሆኑ ገልጠው፣ ቋንቋ፣ ጎሳ የማይል የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ፣ ለሁሉም በማድረስ፣ ያቢያተ ክርስትያናት ውኅደትና አንድነት በምተሰጠው የሓዋርያዊ ኖልዎ አገልግሎት እንዲረጋገጥ እያነቃቃች፣ ሌላውን ለመቀበል የሚገፋፋው እሰይታ እንዲስፋፋ አብነት በመሆን የእግዚአብሔር ፍቅር ትመሰክራለች” ብለዋል። በመጨረሻም የቤተክርስትያን ሓዋርያዊ ተልእኮ በማስመልከት “መወያየት እና ማብሰር በተሰኙት መመሪያዎች አማካኝነት የእግዚአብሔር ክብር በሁሉም ዘንድ እንዲያበራ የርሱ የፍቅር መግለጫ በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር ታቅረባለች ብለዋል








All the contents on this site are copyrighted ©.