2009-06-03 20:21:39

ቡርኪና ፋሶ


RealAudioMP3 በቡርኪናፋሶ ባለፉት 10 ዓመታት ያልታየው ኃይለኛ የኵፍኝ በሽታ ካምስት ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑትን የሕጻናት ሕይወት እየቀጨ መሆኑ ተገልጠ። በዚህ ወረርሽኝ በሽታ ሳቢያ 300 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው እና ሌሎች 45 ሺሕ በበሽታው መለከፋቸው ያገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መገልጫ አስታውቀዋል።

በበሽታው ሳቢያ የሚሰቃየው ሕዝብ አለ ድንበር ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የሓኪሞች ማኅበር የሕክምና ድጋፍ እየቀረበለት መሆኑ ሲነገር። በክልሉ የሕክምና መስጫ እጥረት ሳቢያ፣ በበሽታው ከተለከፉት ውስጥ 10% ለሞት አደጋ እየተጋለጠ መሆኑም የሓኪሞች የግብረ ሰናይ ማኅበር ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። ያለ ድንበር የሐኪሞች የሕክምና ጣቢያ በሳምንት 850 በዚህ በሽታ የተለከፉትን እንደሚያስተናግድም በብሩኪናፋሶ የዚህ የሐኮሞች የግብረ ሠናይ ማኅበር ተጠሪ ፍራንሲስ ጂደይ በመግለጥ፣ በሽታው በእጅጉ ሊስፋፋ እንደሚችልም ያሠጋል ማለታቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.