2009-06-01 17:42:19

የሁሉም ሃይማኖት ምእመናን ሴቶች በጋራ


RealAudioMP3 በኢጣሊያ የሁሉም ሃይማኖት ምእመናን ሴቶች የሚያቅፍ የጋራ ድረ ገጽ ከባለፈው ግንቦት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ላገልግሎ መዋሉ ተገለጠ። በኢጣሊያ ሰላማዊ ውኅደትና ማህበራዊ ኑሮ እውን እንዲሆን ዓልሞ የተሠራ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል የሰባአዊ መብትና ፈቃድ መከበር ቅስቀሳ እንደሚያካሂድም ተገልጠዋል።

የሴቶች የሕጻናት መብት ጉዳይ ቀርቦ የሚከታተል መሆኑም ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። ዓለም አቅፍ የሁሉም ሃይማኖት ምእመናን ሴቶች ግሎባል ዎማን ኦፍ ፋይዝ ለተተሰኘው አለም አቀፍ ማኅበር ቅርጫፍ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ ሰላምን የሚያነቃቃው ማኅበር አለ ምንም አድልዎ የመብት እኩለት በሁሉም መስክ እንዲረጋገጥ የሚያነቃቃ ብቻ ሳይሆን በሴቶች ና በሕጻናት ላይ የሚደርሰውን በደል ገሃድ በማውጣት ለመብትና ፈቃድ የሚከራከር ጭምር መሆኑ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.