2009-06-01 17:43:00

በድኽነት ለሚጠቁት ቤተሰብ ድጋፍ


RealAudioMP3 ትላትና በመላ ኢጣሊያ ቍምስናዎች የተሰበሰበው ምጽዋት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ቤተሰቦች መርጃ እንደሚውል ተገለጠ። የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በዚህ ባለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ ለተጠቁትና በድኽነት ለሚገኙት ሁሉ የኤኮኖሚ ድጋፍ ለማቅረብ ከኢጣሊያ የባንክ ቤቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ያነቃቁት የድጋፍ ዕቅድ በተመለከተ የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ የኤኮኖሚ ጽ/ቤት ተጠሪ ብፁዕ ኣቡነ ጃምፒየሮ ፋሳኒ “ሌላው እየተሰቃየ ዝም ብሎ ማየት የክርስትያን መንፈስ ኣይደለም፣ ጸረ ሰብአዊነትም ነው። ቤተ ክርስትያን ምጽዋት ለተለያዩ የሰብአዊ እቅዶች በተለይ ደግሞ ለድኾች መርጃ ማዋል ተቀዳሚውና ጥንታዊው ዓላማዋ ነው፣ ስለዚህ ሌላው እየተሰቃየ እንዳላዩ ሆኖ መኖር ክርስትያን መሆናችንን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነታችንም የሚጻረር ተግባር ነው፣ ቤተ ክርስትያን ማለት በተለያዩ ምክንያቶች ለሚሰቃየው ሁሉም ቅርብ መሆን ማለት ነው፣ ክርስቶስ የእኛ ሕይወት ተካፋይ በመሆን ያሳየው ፍቅር ቤተ ክርስትያን ትመሰክረውም ዘንድ ኃላፊነት ኣላት” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.