2009-06-01 17:43:24

ሕጻናት እንደ ቅ.ጳውሎስ ልኡካነ ወንጌል


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ቅዳሜ “ሕጻናት እንደ ጳውሎስ ልኡካን” በተሰኘው በዓል የሕጻናት የተልእኮ ተግባር ኣባላት የሆኑት 7 ሺሕ ሕጻናት ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ።

የሕጻናት የተልዕኮ ተግባር ኣባላትን የመሩት የአሕዛብ የስብከተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንት ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ መሆናቸው ሲታወቅ። ቅዱስነታቸው ሕጻን የነበሩበት ዘመን ከግል ታሪክ ጋር በማያያዝ ለጉባኤው መልእክት በማስተላለፉ ካንዳንድ ሕጽናት ለቀረበላቸው ጥያቄም መልስ መስጠታቸው ተገልጠዋል።

ለቀረቡላቸውም ጥያቄ ሲመልሱ፣ “ር.ሊ.ጳ. እሆናለሁ ብየ አስቤውም አላውቅም እንደናንተ ሕጻን ነበርኩ፣ መጫወት መሳቅ መጣላት፣ ሕጻን ሆኜ አንድ ሕጻን የሚኖረውን ሁሌ አሳልፊያለሁ፣ ይቅር የመባባል የመታረቅ መንፈስ ጨርሶ ከኛ መራቅ የለበትን” ብለዋል። “ባንዲት በጀርመን አገር በምትገኘው በአሁኑ ወቅት ብዙ በማትታወቀው መንደር መወለዳቸው ገልጠው፣ እግዚአብሔር እንዴት ለዚህ አቢይ የኃላፊነት ጥሪ እንደመረጠኝ በጣም ነው የሚደንቀኝ፣ ምንም’ኳ ይህ ኃላፊነት ካቅሜ በላይ ቢሆንም በእርሱ ድጋፍና ከለላ በመታመን ከእርሱ እጅ ኃላፊነቱን እሺ” በማለት እንደተቀበሉት አብራርተዋል።

በመጨረሻም “እለታዊ ሕይወታችንን በጸሎት ጀምረን በጸሎት ልንደመድመው ይገባናል፣ እሁድ በቅዳሴ መሳተፍ በየእለቱ ለምናደርገው ጸሎት መሠረት ነው” ብለዋል። “በእለተ ሰንበትን በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የመሳተፉ ልምዱ ከሌለን ለሳምት የሚሆነን መንፈሳዊ ድጋፍ በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት በመሳተፍ ካልተቀበልን፣ ሕይወታችን ትርጉሙ አይኖረውም” ብለዋል።

“ሁሉም በፍቅር ሥራ የመትጋት ክርስትያናዊ ኃላፊነት እንዳለበትም አስገንዝበው፣ በመደጋገፍና ለሌላው በማሰብ የእግዚአብሔር ፍቅር ሕያው በማድረግ ፍቅሩን መመስከር ይገባናል፣ ይህ ፍቅር አለ ምንም አድልዎና ልዩነት ሌላውን እንደ ራሱ ለመቀበል እንድንችል ያግዘናል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.