2009-06-01 17:43:46

 


RealAudioMP3 የወቅቱ ያኗኗር ስልት ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ የሚያጠብ ብሎም የሚሰርዝና ወላጅ እና ልጅ የሚያራርቅ መሆኑ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሮማ ካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ቀን ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ፣ የሕይወት ክብርና እሰይታ ወላጆች ለልጆቻቸው የማስተላለፉ ብቃት እያጠራቻው አብነት በመሆን ጥሪ እየደከሙ፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የጥሪ ኃላፊነት እየዘነጉ መሆናቸው የሚመሰክሩ የተለያዩ ማኅበራዊና ሰብአዊ፣ ባህላዊና ፖሊቲካዊ ነክ ተግባሮችን ዘርዝረው፣ ወቅቱ የትምህርት አሰጣጥ ሂደት እጅግ ላደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ አሳስበው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸንን ጉዳይ መሠረት በማድረግ የኢጣሊያ የወላጆች እንቅስቃሴ ተጠሪ ኤሊሳቤታ ስካላና በኢጣሊያ የቨረኖ ሰበካ የወላጆች ሓዋርያዊ ኖልዎ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ ፒየሮ ደለ ቨዶቨ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “እናት ኣባት በሥራ የተጠመዱ በመሆናቸው ዕለታዊ ኑሮ ለማሸነፍ የሚደረገው ሩጫ ወላጅና ልጅ የሚያራርቅ፣ ላንድ አፍታ ብቻ እንዲገናኙ እያደረገ እውነተኛ ውይይት ወይንም ግኑኝነት እንዳይኖር እያደረገ ነው” በማለት፣ “ሁሉም ግዜ የሌለው በመሆኑ ልጆች ለማነጽ ሳይሆን በሥራ እንዲጠመዱ የማድረጉ ልምድ እየተከተሉ ለልጆች የተሟላ ሕንጸት ለመስጠት ቀርቦ የመከታተሉና በሕይወት ክብር የማነጹ ኃላፊነት እየቀረ ነው”። ስለዚህ “ይህ አይነቱ አደገኛው ባህል በወላጆችና ልጆች መካከል ተከስቶ ያለው ክፍተት ለመቅረፍ በቅድሚያ ለወላጆች ሕንጸት መስጠት ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ወላጆች ልጆቻቸውን በማነጽ ረገድ ያላቸው ሚና በተሰኘ ርእሥ አቭሲ የተሰኘው መንግታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እድገት የሚደገፍና የሚያነቃቃ ማኅበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ስብሰባ በቤተልሔም እየተካሄደ መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ከሰጠው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.