2009-05-29 15:23:16

ኮንጎ


RealAudioMP3 በዴሞክራሲያዊት ሬፑብሊክ ጎንጎ ሰሜናዊ ክልል የሚኖረው ህዝብ በሁለት የውጭ ታጣቂ ህይሎች እነርሱም የኡጋንዳው የጌታ ስራዊት በማለት እራሱን በሚጠራው ግንባርና የሩዋንዳው ዴሞክራሲያዊ ኃይል ለሩዋንዳ ነጻነት በሚል መጠሪያ የሚታወቀወ ታጣቂ ኃይል አማካኝነት ላደጋ መጋለጡ ይነገራል።

የዱንጉ ዶርማ ሰበካ አስተዳዳሪ አባ አንድረ ዋሊያ በአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ድረ ገጽ አማካኝነት የሰጡት መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት እንዳሚያመለክተው፣ በነዚህ የውጭ አገር ታጣቂ ኃይሎች አማካኝነት የዚህ የሰሜን ዴሞክራሲያዊት ሬፑብሊክ ኮንጎ ነዋሪው ሕዝብ ቤቱንና ንብረቱ እየተወ ለመፈናቀል አደጋ እየተጋለጠ መሆኑ ታውቀዋል።

የኮንጎ በተፈጥሮ የማዕድን ሃብት ክልል ለመቆጣጠር ያቀዱ የውጭ ኃይሎች ጥቃት የክልሉ ሴቶች ለወሲብ አመጽ፣ ሕዝቡ ለተለያዩ የግዳጅ ሥራዎች ተጋልጦ፣ ቤቱን እና ንብረቱ እየተነጠቀ መሆኑም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.