2009-05-29 15:15:57

ስለ ጥሪ የሚሰጥ ድጋፍ


በአሲዚ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ማኅበር፣ ወጣቶች ጥሪያቸውን ለይተው እንዲያውቁ እና ብለውም ለመከተል የሚያግዛቸው የአምስት ቀናት ሕንጸት እንዲሰጥ ሃሳብ ማቅረባቸው ተገልጠዋል። RealAudioMP3 እቅዱን አስመልከተውም የዚህ የሕንጸት መርሃ ግብር ጀማሪና ተጠሪ አባ ጆቫኒ ማሪኒ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያስረዱ፣ “በቅድሚያ ወጣቱ ጥሪውን ለይቶ እንዲያውቅ ማገዝ ማለት ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ማድረግ ነው። ቀጥሎም የጥሪዎች ስብከተ ወንጌል ማለትም ጥሪህ የእግዚአብሔር እቅድ መሆኑ መለየት፣ እያንዳንዱ በጥሪው አማካኝነትም በታላቁ የእግዚአብሔር እቅድ ተሳታፊ መሆኑ እንዲያውቅ ለመደገፍ ያቀደ መርሃ ግብር ነው” ብለዋል።

“ወጣቱ መሠረታዊ የሕይወት ጥያቄዎች በማቅረብ መልስ ይሻል፣ የሁሉም ጥያቄዎች መልስ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት በመገናኘት ጥሪህን ለይተህ ከመኖር የሚገኝ ነው። ስለዚህ ጥሪህን ለይተህ መኖር ማለት ለመሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሚያግዘውን መንገድ መከተል ማለት ነው” ብለዋል።

“ይኸንን የሚያበረታታና የሚደገፍ የሚመራንም መንፈሳዊ አባት ወሳኝ ነው። መንፈሳዊ አባት በቅድሚያ የእያንዳንዱ ነጻነት የሚያፈቅርና የሚያከብር መሆን ይኖርበታል። ስለዚህ ምርጫዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ መከተል የደስታ መሠረት መሆኑ እንድናውቅ እራሳችንና ሌሎችን ለማወቅና እግዚአብሔር የሕይወታችን ማእከል መሆን እንዳለበት መንገዱን ለይቶ የሚያሳየን በቃልና በተግባር ጥሪህን ከመኖር የሚገኘው ደስታ የሚመሰክር መሆን አለበት” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.