2009-05-29 15:11:12

ሰማዕት ኵይሪኖ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በአራተኛው ክፍለ ዘመን በክሮአሽያ የሲሻ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ቅዱስ ሰማዕት ኵይሪኖ ሰኔ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ለመዘከር የሚከናወኑት መንፈሳዊና ሐዋርያዊ ዕቅዶች ምክንያት በማድረግ ለአገሪቱ ቤተ ክርስትያን በተለየ ለክርክ ሰበካ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ።
RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. በዚህ በክሮአሽያ በክርክ ሰበካ ለየት ባለ መልኩ በሚካሄደው መንፈሳዊ ክብረ በዓል እሳቸውን ወክለው የሚቀርበው መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚመሩት ብፁዕ ካርዲናል ጆሲፕ ቦዛኒክ መሆናቸውም ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና ያመለክታል። የር.ሊ.ጳ. መልእክት እንደሚያመለክተውም ለዚህ ክልል ምእመናን ያላቸውን ቅርበት ለየት ባለ መልኩ ለማረጋገጥ በስማቸው በበዓሉ የሚገኙት የክርክ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቦዛኒች መሆናቸው ታውቀዋል።

ቅዱስ ኵይሪኖ በክርስቶስ ያለውን እምነት በመመስከር የጣዖት አምልኮና መሥዋዕት ማቅረብን በመቃወም፣ በዘመኑ ለነበረው ንጉሥ ጋለሪዮ ባለ መታዘዛቸው ምክንያት ባንገታቸው ኣቢይ ድንጋይ ተንጠልጥሎ በሳቫ ወንዝ ተጥለው እንዲሞቱ መደረጋቸው የቤተ ክርስትያን የሰማዕታት የታሪክ ማኅደር ይመሰክረዋል። ይኸንን የጠቀሰው የር.ሊ.ጳ. መልእክት ቀጥሎም ሰማዕት ኵይሪኖ የቅዱስ ጳውሎስ አብነትን በመከተል በተለይ ደግሞ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች በጻፋት ሁለተኛይቱ መልእክት ላይ በምዕራፍ 4 እንደሚነበበው “የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን….የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና መከራ ተካፋዮች በመሆን የእርሱ ድል ተካፋዮች መሆናችን እንመሰክራለን፣” የሚለውን ጳውሎሳዊ መንፈሳዊነትን በመኖር ሰማዕትነት የተቀበለ ቅዱስ ኵይሪኖ አማላጅነት ለክሮአዚሽያና ለክርክ ህዝብ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቸው ዘንድ እንደሚጸልዩና ምእመናን ሁሉ የዚህ ጸሎት ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ቦዛኒች ምእመናንን ያበረታቱ ዘንድ ቅዱስ አባታችን አደራ ማላታቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.