2009-05-27 17:24:24

ጋሊለዮ ጋሊለዪ


ጋሊለዮ ጋሊለዪ በሥነ ታሪክ ተንተርሶ ዳግም ማንበብ በተሰኘ ርዕስ፣ እዚህ በኢጣሊያ ፊረንዘ ከተማ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ቅድስት መንበር እንደምትሳተፍ ተገልጠዋል። ይህ ጉባኤ 400ኛውን ዓመት ያገባደደው በዓለማውያን እና በካቶሊክ ሊቃውንት መካከል ላለ መግባባት ምክንያት የሆነው የጋሊለዮ ጋሊለዪ የምርምር ጥናቶችን ዳግም በመከለስ አለ መግባባቱ በታሪካዊ ሂደት መተንተንና መግለጡ ከምን ግዜም በበለጠ ዛሬ በእምነትና በምርምር መካከል ያስከተለው አለ መግባባት መፍትሔ እንዲያገኝ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጠዋል።

RealAudioMP3

2009 ዓ.ም. ዓለም አቅፍ የሥነ ከዋክብት ዓመት ተብሎ እንዲታሰብ መወሰኑ የሚዘከር ሲሆን፣ ይኽንን እግምት ውስጥ በማስገባት፣ ፊረንዜ የሚገኘው የኢየሱሳውያን ማኅብር መንበረ ጥበብ የጋሊለዮ ጋሊለዪ ሥራዎች በታሪክ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ ሥነ እውቀቶች መሠረት መተንተን በሚል ርዕስ ሥር በጠመራው በዚህ ዓውደ ጥናት የኢጣልያ ርእሰ ብኄር ጆርጆ ናፖሊታኖ እንደሚሳተፉም ተገልጠዋል።

ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሜልኮር ሳንቸስ ዴ ቶካ “በሥነ ምርምር ዘርፍ በታሪክ የተከሰቱት በተለይ ደግሞ ከጋሊለዮ ጋሊለዪ ሥነ ምርምር ጋር የተፈጠረው አለ መግባባት ለማስወገድ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባዔ ቀጥለውም ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በማሳሰብ፣ አንዱ ሌላውን ማውገዝ ሳይሆን በመቀራረብ መወያየት እንደሚያስፈልግ እየታመነበት በመምጣቱም በእምነትና በምርምር መካከል ያለው ልዩነት ከመቀራረብ የሚፈልቅ ከሆነ የሚደጋገፉ ይሆናሉ ሆኖም ግን ልዩነት አንዱ ሌላውን ከማግለል የሚከሰት ከሆኑ የሚጻረሩ አንዱ ሌላውን የሚያገል ይሆናል፣ ስለዚህ ይህ የሚካሄደው ዓውደ ጥናት በዚህ መሠረታዊው የሥነ ጥበብ መርህ የተሸኘ ይሆናል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.