2009-05-27 17:03:48

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናን የተለመደውን የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ ጉባዔ አስተምህሮ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው በጣሊያንኛ ሰፋ ያለ አስተምህሮ ካቀረቡ በኋላ ለእንግሊዝኛው ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚከተለውን አጭር አስተምህሮ አቅርበዋል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በዛሬው ትምህርት ክርስቶስ ስለ ገዳማዊው ሊቅ ቅዱስ ተዮዶር ሕይወትና ትምህርት የምንመለከተው ነገር ወደ መካከለኛው የባይዛንቲን ዘመን ተመልሰን እንድናስብ ያደርገናል። ቅዱስ ተዮደር በ759 ዓ.ም. ከሃብታምና ልዑላን ቤተሰብ ተወልዶ ሃያ ሁለት ዓመት ሲሞላው ወደ ገዳም ገባ። ቅዱስ ተዮዶር ፀረ ቅዱስ ምስሎች ንቅናቄን “የክርስቶስ ምስል ማስወገድና መስበር የማዳን ሥራውንም አብሮ ማስወገድና መቃወም ነው” ሲል በእጅጉ ይከራከር ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ተዮዶር የገዳም ሕይወት አስተዳደር ሥርዓተ ደምብና መንፈሳዊ ጉዳዮች በሚመለከት ፍጹም ለውጥና ተሓድሶ ጀምሮአል።








All the contents on this site are copyrighted ©.