2009-05-27 17:37:33

እገዛ ለምትሰቃይ ቤተ ክርስትያን የግበረ ሠናይ ማኅበር


እገዛ ለምትሰቃይ ቤተ ክርስትያን የተሰኘው ዓለም አቀፍ የግብረ ሠናይ ማኅበር እ.ኤ.አ. የ2008 ዓ.ም. ዓበይት ክንዋኔዎቹን የሚዳስስ ሰነድ በይፋ እንዳቀረበ ተገለጠ። RealAudioMP3 ይህ ሰነድ በማኅበሩ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ፒየር ማሪየ ሞረል አማካኝነትበይፍ በቀረበበት ዕለት አጋጣሚም የግብረ ሠናይ ማኅበር እ.ኤ.አ. እስከ 2012 ዓ.ም. የሚከተላቸውን ዕቅዶች ተገልጠዋል። ሰነዱ እንደሚያመለክተውም ይህ የግብረ ሠናይ ማኅበር በ 2008 ዓ.ም. በ17 የተለያዩ አገሮች በ82 ሚሊዮን ኤውሮ የሚገመት ዕቅዶች እተግባር ላይ ማዋሉ ሲነገር፣ ሰባት ሚሊዮን ኤውሮ ከኢጣሊያ ከ16 ሺህ የተለያዩ መልካም ፍቃድ ካላቸው በጐ አድራጐት ማኅበራትና ግለ ሰዎች የተሰባሰበ መሆኑ ሲታወቅ፣ እተግባር ላይ ከዋሉት ዕቅዶችም 27.5% ለመንፈሳዊና ለሃይማኖት አገልግሎት የሚውሉ የሕንጻ ግንባታዎች፣ 13.7% ለቲዮሎጊያ መንበረ ጥበባት ድጋፍ፣ 9.5% ለትምህርተ ክርስቶስ ማስፈጸሚያ፣ 7.7% ለሐዋርያዊ አገልግሎት ላለሙ የመገናኛ ብዙኃን ድጋፍ መዋሉ ሰንዱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.