2009-05-27 17:38:51

ናይጀሪያ


RealAudioMP3 የናይጀሪያ ወታደሮች ሜድ በመባል የሚጠሩት ያገሪቱ የኒጀር ደልታ ነጻ አውጭ ተዋጊ ኃይሎችን ለማጥፋት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘረ መሆኑ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት እንዳመለከትው፣ 90% ሴቶችና ሕጻናት የሚገኙባቸው 3 ሺሕ ሕዝብ መፈናቀሉ ታወቀዋል። በዚህ ውጊያ ሳቢያ ለተጎዳው ህዝብ እርዳታ ለማቅረብ ያለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበርና የዚሁ ማኅበር በናይጀሪያ ይሚገኘው ቅንርጫፉ የአገሪቱ የመከላከያ ኃይሎች እየሰነዘሩት ያለው ጥቃት ያቋርጡ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

የናይጀሪያ የመከላከያ ኃይል በዚህ ሜድ በመባል በሚጠራው ግንባር እጅ ተጠልፈው የነበሩት 20 ሰዎች ነጻ እንዳስለቀቀም ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። የተዋጊው ኃይል እየተሰነዘረበት ላለው ጥቃት የተለያዩ የነዳጅ ድፍድህ መምጠጫዎችና ማጣሪያዎችን በማገየት ግብረ መልስ እንደሚሰጥበት፣ በይፋ ማስታወቁ ከክልሉ የሚሰራጩ የዜና ምንጮች ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.