2009-05-25 19:07:19

የሶማሊያ የወቅቱ ሁኔታ


RealAudioMP3 የሶማሊያ ርእሰ ከተማ ሞቃዲሾን ለመቆጣጠር ዓማጽያን እስላማዊ ተጣቂ ሃይሎችና የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት ወታደሮች መካከል እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. የተከፈተው ጦርነት መጠነ ሰፊ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል። ሞቃዲሾ ለመቆጣጠር ግጭቱ አንድ ካለበት እለት ጀምሮ 200 ሰዎች ለሞት መድረጋቸውና ሌሎች 500 የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ሲነገር፣ በብዙ ሺሕ የሚገመተው ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ መጋለጡም ይነገራል።

ጉዳዩ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እጅግ እያሳሰበ መምጣቱ ሲነገር፣ ግንቦት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ያፍሪቃ ህብረት የተባበሩት መንግሥታት ስለ ጉዳዩ መፍትሔ ያፈላልግ ዘንድ ጥሪ ማስተላለፉም ተገልጠዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የተፈናቃዮችና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድረገት ባለፈው ዓርብ ብቻ 8 ሺሕ ሰላማዊ ሕዝብ መፈናቀሉና በጠቅላላ ግጭቱ ከተጀመረበት ወዲህ 57 ሺሕ ሕዝብ መፈናቀሉ ካሰራጨው መገለጫ ለማወቅ ተችለዋል።

አለ ድንበር የሐኪሞች የግብረ ሠናይ ማኅበር በኢጣሊያ ላለው ቅርንጫፍ ተጠሪ ኮስታስ ሞስኮሪቲስ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “የሶማሊያው የእርስ በእርሱ ግጭት እየከረረ መምጣቱንም ጠቅሰው፣ ብዙ ሕዝብ ለመፈናቀልና ለምግብ እጥረት አደጋ እየተጋለጠ ነው። እ.ኤ.አ. በዚህች አገር ከ 1991 ዓ.ም. በተቀጣጠለው የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ ብዙ ሕዝብ በኬንያ በስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንደሚገኝ ነው” ብለዋል።

“በሶማሊያ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ጭምር ህዝቡ ጦርነት ካለበት ክልል ለቆ ለመውጣት ችግር እያጋጠመው መሆኑ ገልጠው፣ በክልሉ ያለው የሰብአዊ ጉዳይ ችግር የከፋ፣ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ የግብረ ሠናይ ማኅበራት ለብቻቸው የሚጋፈጡት አይመስልም” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.