2009-05-25 19:06:34

በሮማ አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን


RealAudioMP3 በቀዳሚው ዘመን በነበረችው ቤተክርስትያን ታሪክ ቀደምት የእምነት ሰማዕት ተብለው ከሚጠቀሱት ቀደምት ሰማዕታት ቅድስት ካተሪና ዘ አለክሳድሪያ መሆኗ የቤተክርስትያን ታሪክ የሚገልተው ሲሆን። በዚህ የእምነት ሰማዕት ስም የሚጠራው አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን እ.ኤ.አ. እሁድ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሮማ ከተማ መባረኩ ተገለጠ።

በሩሲያ የፓትሪያርክ የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ ሥርዓት መሪዎች የሊጡርጊያ ሊቃውንት ካህናትና ዲያቆናት እዚሁ ሮማ ቤተ ክርስትያኗ ለመባረክ በተካሄደው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በመምራት መሳተፋቸው ለማወቅ ተችለዋል።

የቅዱስ ዮሓንስ አፈወርቅ አኰቴተ ቍርባን መሠረት ባረገው መስዋዕተ ቅዳሴ፣ የተሳተፉት የክርስትያን አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር እና የዚሁ ምክር ቤት ዋና ፀሓፊ ብፁዕ አቡነ ብሪና ፋረል የብፁዓን ካርዲናላት አፈ ጉባኤ ምክትል ብፁዕ ካርዲናል ሮዠር ኤትቻጋራይ ሌሎች ብፁዓን ጳጳሳትና የካቶሊክ ቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ተጠሪዎችና አባላት መሳተፋቸው ለማወቅ ተችለዋል።

በኢጣሊያ የፈደራላዊት ሩሲያ ልኡከ መንግሥት የሮማ ከንቲባ እና የኢጣሊይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የክርስትያኖች አንድነትና የሁሉም ሃይማኖት ውይይት የሚያነቃቃው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸንሶ ፓሊያ መገኘታቸው ተገልጠዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.