2009-05-25 19:06:01

ር.ሊ.ጳ የሞንተካሲኖን ገዳም ጐበኙ


ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ ሞንተካሲኖን ማለት የቅዱስ በነዲክቶስና የእህቱ የቅድስት እስኮላስቲካ አገርን መጐበኘታቸው ተመለከተ። ቅዱስነታቸው ትናንት እዚህ ጣሊያን አገር ላዚዮ ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኘውን የሞንተ ካሲኖ ከተማና ሰበካ በጐበኙበት ጊዜ በከትማዋ ዋና አደባባይ ፒያሳ ሚራንዳ ከሃያ ሺ በላይ ምእመናን የተሳተፉበት መሥዋዕት ቅዳሴ አቅርበው ስብከት አሰምተዋል፣ የንግሥተ ሰማያት ማርያማዊ ጸሎትም መርተዋል። RealAudioMP3

በዋና አደባባዩ ላይ ባሳረጉት ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት በተለይ ሞንተካሲኖ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ሰለባ ከተማ መሆኑዋን ጠቅሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.