2009-05-25 19:07:01

43ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን


RealAudioMP3 ትላንትና 43ኛው ዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን ታስቦ መዋሉ ተገለጠ። ቀኑን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና ግኑኝነቶች፣ ለአዲስ የመከባበር የመወያየትና የወዳጅነት ባህል ማነቃቂያ፣ በሚል ርእሥ ቀኑን ምክንያት በማድረግ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲታወቅ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግም “Pope2you” የተሰኘ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያንና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከወጣቱ ጋር የሚወያዩበት አዲስ ድረ ገጽ በይፋ ላገልግሎት መዋሉና በብዙ ህዝብ እየተጎበኘ መሆኑ ተገልጠዋል።

የመገናኛ ብዙኀን ጉዳይ የሚንከባከብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማሪያ ቸሊ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት አስመልከትው ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “መልእክቱ ያዳዲስ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚው የኅብረተሰብ ክፍል ላይ ያተኮረ ቢሆንም ቅሉ ለሁሉም የሚናገር ነው” ብለዋል። “በመልእክቱ ማጠቃለያም በቀጥታ የካቶሊክ ወጣቶችን የሚመለከት ሀሳብ የሠፈረበት ሆኖ፣ ወጣት ካቶሊክ በሁሉም ዘርፍና በተለይ ደግሞ ባዳዲስ የቴክኖሎጂ ወጤቶች ተጠቃሚነቱ ላዲስና የመልካም ዜና አብሳሪነት ያውለው ዘንድ አደራ የሚል ነው” ብለዋል።

በጠቅላላ የቅዱስ አባታችን መልእክት “የመገናኛ ብዙኀን ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረ መሆኑ በተለያየ መልኩ የሚያበሥር እና በዚህ ቅዱስ ክብር ዙሪያ አስተንትኖ እንዲደረግበትም የሚያሳስብ ነው” ብለዋል።

የቅድስት መንበር የማኅተምና የዜና ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ አስተዳዳር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የር.ሊ.ጳ. መልእክት “በተለያየ መስክ በተለይ ደግሞ በቴክኖሎጂው ረገድ በፍጥነት እየመጠቀ ያለው ዘመናችንን እግምት ውስጥ ያስገባና የዚህ ፈጣኑ ለውጥ ዓለም የቴክኖሎጂው ዕድገት ለመከባበር ለመወያየትና ለወዳጅነት ባህል መስፋፋት መሣሪያ ይሆን ዘንድ የሚያሳስብ ነው” ካሉ በኋላ፣ ቀጥለውም “የሁሉም ኃላፊነትን የሚያነቃቃና የዚህ ዕድገት ተጠቃሚው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ለብቻው እንዳይተውና በተጠቃሚነቱ ዘርፍ ሊደገፍና ባግባብ እንዲጠቀምበትም ሕንጸት ማግኘት እንዳለበት የሚያሳብ መሆኑ” አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.