2009-05-22 16:19:21

የብፁዕ አቡነ ክረፓልዲ “እግዚአብሔር ወይስ ጣዖት “ የተሰየመ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡


በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጃምፓውሎ ክረፓልዲ የደረሱት “እግዚአብሔር ወይም ጣዖት” የተሰየመ መጽሐፍ ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ትገልጠዋል።

ከግረጎርያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የደረሰ ዜና እንዳመለከተው ፡ መጽሐፉ ለአራት ክፍሎች የተከፋፈለ መሆኑ እና ፡ እምነት አእምሮ ፖሊቲካ እና ሰብአዊ መብቶች የሚያንጸባርቅ መጽሐፍ መሆኑ ተመልክተዋል።

የመጽሐፉ ደራሲ በቫቲካን የፍትህሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጂምፓውሎ ክረፓልዲ በቃለ ምልልስ መልክ እንደገለጹት፡ የመጽሐፉ አርእስት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ካደረጉት ስብከት የተውሰደ መሆኑ ጠቅሰው ፡ ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ላይ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ከሕይወቱ እና ከማሕበራዊ ኑሮው ካራቅ እና አላስጠጋም ካለ በጣዖት ላይ ይወድቃል ያሉትን የመጽሐፉ መሠረታዊ መነሻ መሆኑ አስገንዝበዋል።

በጣዖት ማምለክ ማለት የሰው ልጅ ነፃነት ሐላፊነት እና እድገት መነጠቅ ባዶ መሆን መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በግዜው ያደረጉት ስብከት መግለጣቸው ብፁዕ አቡነ ጃም ፓውሎ ክረፓልዲ አስታውሰዋል።

ብፁዕ አቡነ ጃምፓውሎ ክረፓልዲ የደረሱት እግዚአብሔር ወይስ ጣዖት የተሰየመ መጽሐፋቸው በሰናይ እና እኩይ መሃከል ያለው ልዩነት የሚያብራራ መጽሐፍ የህሊና ዕረፍት የሚሰጥ መጽሐፍ ሆኖ የስው ልጅ የመምረጥ ዕድል እንዳለው የሚያስረዳ መጽሐፍ መሆኑ በቃለ ምልልስ መልክ መግለጣቸው ታውቆዋል።

የሰው ልጅ ፖሊቲካው ኤኮኖምያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች ሲደቀኑበት፡ መፍትሔ ለመሻት የሰው ወዳጅ በሆነ እግዚአብሔር ቢጠጋ እንደሚሻለው ያመለከቱት የመጽሐፉ ደራሲ ፡ ይህ ሲባል ቤተ ክርስትያን ለፋይናንሳዊ እና ኤኮኖምያዊ ችግሮች ተክኒካዊ መፍትሔ አላት ማለት ሳይሆን፡ መፍትሔዉ ከቅዱሳን ወንጌሎች ከተወሰደ የቤተክርስትያን ትምህርት ላይ በመመርኰስ ሞራላዊ ፍርድ ትሰጣለች ማለት መሆኑ መግለጣቸው ተነግረዋል።

የውቅቱ ዓለም አቀፍ ኤኮኖምያዊ እና ፋይናንሳዊ ቀውስ ብንወስድ የዚሁ ቀውስ ሐላፊነት የሚሸከመው ፓሊቲካ ነው ፡ ግብረ ገብነት የለሽ ኤኮኖምያዊ እና ፋይናንሳዊ ሂደት ውድቀት እንደሚያስከትል መታየቱ እግዚአብሔር ውይስ ጣዖት ርእስ ያደረገ መጽሐፍ ደራሲ በቫቲካን የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጃም ፓውሎ ክረፓልዲ ማመለክታቸው ታውቆዋል።

ማኝኛውም ነገር ፈሪሐ እግዚአብሔር የሌለው እና ስስት ላይ የተመረኰሰ ስራም ሆነ ሕይወት ጠናማ ሊሆን እንደማይችል ያመለከቱ ብፁዕ አቡነ ክረፓልዲ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ሃያ ሶስተኛ “pacem in terris” ሰላም በምድር የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክትም ስነምግባር ለሰላማዊ ኑሮ እንደሚጥይቅ አሳታውስዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ በቅርቡ እንዲያወጡት የሚጠበቀው፡ ሐዋርያዊ መልእክትም የወቅቱ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ እና ሥራ እና የሰራተኞች መብት እንደሚያወሳ ብፁዕ አቡነ ክረፓልዲ የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ መግለጣቸው ተነግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.