2009-05-22 15:02:04

የቅዱስ ኤጂድዮ መስራች የካርሎ ማኞ ሽልማት ተቀበሉ፡


በሮማ የቅዱስ ኤጂድዮ ማሕበረ-ሰብ መስራች እና የታሪክ ጠቢብ ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ ፡ በጀርመን አኲስ ግራና ማለት አኸን ላይ የካርሎ ማኞ አገሮች አቀፍ ሽልማት መቀበላቸው ከዚሁ ቦታ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ዜናው እንደመልከተው ፡ ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ ሽልማቱ የተቀበሉበት ምክንያት፡ ኤውሮጳ ውስጥ በኅዝቦች መሃከል መረዳዳት እና ትብብር እንዲከሰት ሰብአዊ እና ሰላማዊ ሕይወት ግሃድ እንዲሆን ባለማቋረጥ ባካሄዱት ያለሰለሰ ጥረት ነው።

ከዚህ ባሻገር ፕሮፈሶሩ በዚች ዓለማችን ላይ ፍትሐዊ እና ሰላማዊ ኑሮ እንዲገኝ የተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች የሚከተሉ የዓለም ህዝቦች ለማቀራረብ እና ለማጣጣም ሳይታክቱ እንደሚጥሩ በተለያየ ግዝያትም ጥረታቸው መሳካቱ ዜናው አብራርተዋል።

ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ ሮማ ላይ የመሰረቱት ቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ ፡ በተለያዩ ሃገራት በተለይ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የሚከሰቱ ግጭቶች ለማርገብ እና ብሎም ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ታትሮ የሚሰራ ማሕበረሰብ መሆኑ የማይዘነጋ ነው።

ይሁን እና ከአሁን በፊት የካርሎ ማኞ አገሮች አቀፍ ሽልማት ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለጀርመን ዜጋ የመጀመርያ ቻንስለር ኮንራድ አደናወር ለየጣልያኑ የፖሊቲካ ሰው አልቺደ ደጋስፓሪ መሰጠቱ የሚታውስ ነው ።

ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ የተሰማቸውን ደስታ መግለጣቸው ከአኲስ ግራና ማለት ከአኸን ተመልክተዋል።

ካርሎ ማኞ በማእከላዊ ዘመን ጠቅላላ ኤውሮጳ ያስተዳደሩ እና ለአረማውያን ክርስትና ያስተዋወቁ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኤውሮጳ የነበሩ ናቸው።








All the contents on this site are copyrighted ©.