2009-05-22 17:26:01

የሶማሊው ውጥረትና ተፈናቃዮች


RealAudioMP3 በሶማሊያ በእስላማዊ አክራሪያን ታጣቂ ኃይሎችና ለሽግግር መንግሥት ታማኝ ወታደሮች መካከል ያለው ውግያ አሁንም እየቀጠለ ነው። ሁኔታው በሰብአዊ ጉዳይ እያስከተለው ያለው የከፋው ችግር ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እጅግ እያሳሰበ መሆኑ ተገለጠ። አለ ድንበር የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሐኪሞች የግብረ ሠናይ ማኅበር መግለጫ መሠረት፣ 300 ሺህ ሕዝብ መፈናቀሉ እና በነዚህ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ 45 ሺሕ ሕዝብ መቃዲሾን ለቆ መፈናቀሉ ለማወቅ ሲቻል፣ በኬንያ ክልል ባለው የሶማሊያ ተፈናቃይ ሕዝብ መጠለያ ሠፈር በተፈናቃይ ሕዝብ ከመጨናነቁም አልፎ በቂ የሰብአዊ እርዳታ የሌለውም በመሆኑ፣ ብዙዎች ግጭቱ ወደ አለበት የአገራቸው ክልል ለመመለስ እንደሚሹ ታውቀዋል።

አለ ድንበር የሐኪሞች የግብረ ሠናይ ማኅበር በኢጣሊያ ላለው ቅርንጫፍ ተጠሪ ኮስታስ ሞስኮኮሪቲስ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “የሶማሊያው የእርስ በእርሱ ግጭት እየከረረ መምጣቱንም ጠቅሰው፣ ብዙ ሕዝብ ለመፈናቀልና ለምግብ እጥረት አደጋ እየተጋለጠ ነው። እ.ኤ.አ. በዚህች አገር ከ 1991 ዓ.ም. በተቀጣጠለው የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ ብዙ ሕዝብ በኬንያ በስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንደሚገኝ ነው” ብለዋል።

በሶማሊያ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ጭምር ህዝቡ ጦርነት ካለበት ክልል ለቆ ለመውጣት ችግር እያጋጠመው መሆኑ ገልጠው፣ “በክልሉ ያለው የሰብአዊ ጉዳይ ችግር የከፋ፣ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ የግብረ ሠናይ ማኅበራት ለብቻቸው የሚጋፈጡት አይመስልም” ብለው፣ አክለውም “በግጭቱ ሳቢያ የመቁሰል አደጋ ላጋጠማቸው ይህ አለ ድንበር የተሰኘው የሐኪሞች ማኅበር የሕክምና እርዳታ እየሰጠ መሆኑ” ጠቅሰው “ባለፈው ሳምንት በአንድ ከሞቃዲሾ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክልል ባለው የማኅበሩ የሕክምና ጣቢያ ብዙ ሕጻናትና ሴቶች የሚገኙባቸው የመቁሰል አደጋ ላጋጠማቸው ለ 112 ዜጎች የሕክምና እርዳታ ሰጥተዋል” በሞቃዲሾ የነበረው የሐኪሞች ማህበር የቀዶ ጥገና ሕክምና ጣቢያ በክልሉ ባለው የጸጥታና የደኅንነት ችግር ምክንያት መዘጋቱንም አስታውሰዋል። “የግጭቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሰላማዊው ሕዝብና ባገሪቱ የሚገኙት የተለያዩ ያለም አቀፍ የእርዳታ ማኅበራት ለአደጋ ከማጋለጥ እንዲቆጠቡ” አለ ድምንበር የሐኪሞች ማኅበር ጥሪ አቅርበዋል። በኬኒያ የስደተኞችና ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር ላሉት የሶማልያ ዜጎች በቂ እርዳታ ይቀርብለትም ዘንድ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥሪ እያስተላለፈ ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.