2009-05-22 17:25:30

አዲሱ የዌስትሚኒስተር ሊቀ ጳጳሳት


RealAudioMP3 ትላትና የዌስትሚኒስተር ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ኒኮላስ ሢሜተ ጵጵስና በተቀበሉበት የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ባሰሙት ስብከት፣ “ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት እውነተኛውን ደስታ ለማግኘት የእምነት ማኅበራዊው አድማሱና እምነትና ምርምር ያዳገፈ እምነት መሻትና እግዚአብሔርን ፈልጎ ማግኘት ወሳኝ ነው” ብለዋል።

“የእምነት ማኅበራዊነት ማለትም እምነትን በቤተክርስትያን የሚኖር የግል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ጭምር መገለጥ፤ መኖርና መመስከር ያለበት” መሆኑ አስረድተው፣ “ይህ ዓይነቱ እምነትን የመኖሩ ሂደት በማኅበረሰብ ዘንድ ይከበርም ዘንድ አስፈላጊ ነው” ብለዋል። “በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት የጎሳ የባህልና የማኅበራዊ ኑሮ ደረጃ የሚያስከትለው ልዩነት የማይበግረው፣ በማኅበራዊ ሕይወት እንድንመሰክረው ይገፋፋናል፣ ስለዚህ እኔ አምናለሁኝ ብሎ የግል ኅሊና ማርካት ብቻ ሳይሆን፣ የእምነት ውጫዊው ገጽታውንም ጭምር መመስከሩ ወሳኝ ነው። አማኙ ማኅበረሰብና የእምነት ተቋሞች በተለይ ደግሞ ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው አስተዋጽዖ ለማኅበራዊ ጥቅም ያቀና መሆኑ መንግሥት እውቅና በመስጠት ሊያከብረው ይገባዋል” ብለዋል።

በመጨረሻም፣ እምነት እና ምርምር የማይገናኙ እርስ በርሳቸው የማይሟሉ፣ ተቃራኒ ናቸው ብለው የሚያምኑ እንዳሉ አስታውሰው፣ ይህ ደግሞ እውነትን ለመፈለግ የሚደረገው ምርምር የሚጻረርና እውነተኛ መከባበር የተካነው ውይይት የማያነቃቃ ነው” ብለዋል። የመገናኛ ብዙኀን እውነተኛው መከባበር የተካነው ግኑኝነትና ውይይት ማነቃቂያ እንጂ ለግጭት የሚገፋፉ መሆን የለባቸውም” እንዳሉ ተገልጠዋል። በዚህ ለስሜተ ጵጵስና ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የዌስትሚኒስትር ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል መርፍይ ኦኮኖር፣ የአየርላንድ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሲን ብራድይ፣ የስኮትላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ካዝ ኦብራይን፣ የአንግሊካዊት ቤተክርስትያን መንፈሳዊ መሪ ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊሊያምስና ሌሎች 50 ብፁዓን ጳጳሳት፣ 500 ካህናት፣ ከ 2 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን መሳተፋቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.