2009-05-21 07:57:01

የቫቲካን አዲስ ድረ ገጽ


RealAudioMP3 የመገናኛ ብዙኀን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኀላፊነት መሠረት "Pope2you" በተሰኘው መጠሪያ ለወጣቶች ያቀና አዲስ ድረ ገጽ ላገልግሎት እንደሚውል ተገለጠ። ይህ አዲስ ድረ ገጽ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ታስቦ በሚውለው 43ኛው ዓለመ ዓቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን ምክንያት በማድረግም ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙኀን ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት በይፋ እንደሚያስተዋውቀው፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ትላትና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ይህ keቫቲካን ድረ ገጾች ውስጥ አንዱ የሆነው አዲሱ ድረ ገጽ፣ “ዓላማው ቅድስት ቤተ ክርስትያን ከወጣቱ ጋር ገንቢ፤ ክፍትና ተቀባይነት ያለው ውይይት የምታካሂድበት፣ ለዚሁ የማኅበረሰብ ክፍል የምትሰጠው ምክር አስተምህሮና ሕንጸት የሚያጠቃልል መሆኑ” የገለጡት ብፁዕ ኣቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ቀጥለውም “በዚሁ አዲሱ ድረ ገጽ በዋናው ገጹ ር.ሊ.ጳ.ና ወጣት ትውልድ በማስቀመጥ ቤተክርስትያንና ወጣቱን የሚያቀራርብ ነው” ብለዋል።

“የዚህ ዘንድሮ ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን መሪ ቃል፣ “አዳዲስ ዕደ ጥበባትና ግኑኝነቶች” የሚል መሆኑም ብፁዕነታቸው ጠቅሰው “በድረ ገጹ አማካኝነት ቅዱስ አባታችን የውይይት የመከባበር የወዳጅነት ባህል እንዲገነባ ያነቃቃሉ” ብለዋል።

በመጨረሻም ድረ ገጹ አmst ቋንቋዎች ማለትም ጣሊያንኛ እንግሊዝኛ ስፓኒሽ ፈረንሳይኛና የጀርመን ቋንቋ የሚጠቀም መሆኑ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.