2009-05-21 15:25:11

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የፖላንድ ፕረሲደንት ተቀብለው አነጋገሩ፡

 


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ከቀትር በኋላ የፖላንድ ፕረሲዳንት ለኽ አለክሳንደር ካዚንስኪን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ የቫቲካን መግለጫ መሠረት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የፖላንድ ፕረሲዳንት ወቅታዊ የፖላንድ ሁኔታ የቫቲካን እና የፖላንድ መንግሥት ግንኙነት እንዲሁም አገሮች አቀፍ ነክ ጉዳዮች በተመለከቱ ተወያይተዋል።

የፖላንድ መንግሥት መሪ ፕረሲዳንት ለኽ አለክሳንደር ካዚንስኪ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብቻ ሳይሆን ከቫቲካን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና የውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር ተገናኝተው በተመሳሳይ ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው መግለጫው አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.