2009-05-20 14:31:45

‘‘በቤተክርስትያን ማንም ባዳ አይደለም’’: ብፁዕ አቡነ ማሪያ ቨልዮ፡


ባለፈው ሰንበት ከሶስት ቀናት በፊት እዚህ ሮማ ውስጥ በቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራን የሕዝቦች ዕለት ተከብሮ መዋሉ የሚታወስ ሲሆን፡ በቅድስት መንበር የስድተኞች ግብረ ኖልዎ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ በካተድራሉ ተገኝተው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት በቤተክርስትያን ዓይን የውጭ ሰው የሚባል የለም እሷ ማለት ቤተክርስትያን ሁሉንም ታቅፋለች ።

የነፍሰኄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጥቅስ ዘክረው፡ የክርስቶስ ፍቅር በሁሉም ልብ ላይ ይደርሳል፡ ቤተክርስትያንም የብዙ ሕዝብ ቋንቃ ባህል እና ቀለም አቀፍ ናት ማለታቸው ተገልጠዋል።

እዚህ ሮማ ከተማ ውስጥ ብሎም በጣልያን የሚኖሩ የውጭ ሰዎች ክብር እና ምስጋና እንጂ በቁራኛ ዓይን መመልከት ኋላ ቀርነት፣ አለማወቅ እና ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ እኩል መብት እና ክብር የሚገባው መሆኑ ባለመገንዘብ ሊሆን እንደሚችል ብፁዕነታቸው አስገንዝበዋል።
በዘለአለማዊት ሮማ ከተማ የውጭ ዜጎች ህልውና አስፈላጊ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ አልፎ አልፎ በውጭ ዜጎች የሚፈጸመው ዓመጽ እና በደል አስከፊ እና አሳዛኝ መሆኑ ገልጠዋል።
ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ የውጭ ዜጎችን መንከባከብ እርዳታ እና መጠለያ መስጠት እንደምትቀጥልበትም በመቀጠል ማመልከታቸው ተያይዞ ተነግረዋል።

አያይዘው፡ የሮማ ከተማ ነዋሪዎች በቃል ብቻ ሳይሆን በግብር የውጭ አገር ዜጎችን እንዲረዱ እንዲተባበሩ እና የብዙኀን ዝርያዎች አብሮ መኖር ሃብት እንጂ ጉዳት አለመሆኑ እንዲረዱ መማጸናቸው ተነግረዋል።

በዓመት አንድ ግዜ ሮማ ከተማ ውስጥ የሕዝቦች ዕለት በድምቀት ተከብሮ እንደሚውል እና የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ዕለቱን በጸሎት በጭፈራ እና በደስታ በጋራ እንደሚያሳልፉት የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.