2009-05-20 15:28:07

የፓኪስታን ውጥረት


RealAudioMP3 በፓኪስታን በሚገኘው በስዋት ስምጥ ሸለቆ ክልል ያገሪቱ የመከላከያ ህይሎች እየሰነዘሩት ባለው የጸረ ታሊባን ጥቃት ሳቢያ ቤቱንና ንብረቱን እየተወ ለመፈናቀል አደጋ የተጋለጠው 2 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪው ህዝብ ከቤተ ክርስትያን ዓቢይ ድጋፍ እየቀረበለት መሆኑ ተገለጠ።

በኢስላማባድ እና በራዋልፊንዲ ከተማ እየደረሰ ያለው ተፈናቃዩ ህዝብ፣ በተለያዩ የካቶሊክ የግብረ ሰናይ ማኅበራት፣ ካሪታስ በመባል ከሚጠራው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር ጋር በመተባበር ድጋፍ እያቀረቡ ናቸው።

በዚሁ ክልል ያለው ሁኔታ አሁንም የተወጠረ መሆኑ ሲነገር፣ ድጋፍ ለማቅረብ ዓቢይ እንቅፋት መሆኑም ፊደስ የዜና አገልግሎት ለራስ ደኅንነት ማንነታቸው እንዳይገለጥ አደራ ያሉት የዓይን ምስክር ጠቅሶ አስታውቀዋል። የዚህ ዓይነት የከፋና በገፍ የመፈናቀል አደጋ የታየው እ.ኤ.አ በ 1994 በሩዋንዳ መሆኑ የተባበሩት መንግሥታት የተፈናቃዮችና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት ተጠሪ አንቶኒዮ ጉተረስ አስታውቀው፣ ለዚሁ ተፈናቃይ ሕዝብ በቂ ያአስቸኳይ እርዳታ ካልቀረበለት የክልሉ ውጥረት እንደሚባባስ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.