2009-05-20 14:54:17

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት ብዙ ምእመናን ባሰሙት አስተምህሮ በቅርቡ ወደ ቅድስት መሬት አድርገውት ስለ ነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰፊው ገልጠው ምእመናን ለመኸከለኛው ምሥራቅ ቤተክርስትያን እና አገራት ሰላምና ብልጽግና አብረዋቸው እንዲጸልዩ ጠይቀዋል፣ ለጉብኝቱ መሳካት ለተባበሩትና ለረዱት ሁሉም ከልብ አመስግነዋል። RealAudioMP3

በፊታችን እሁድ በቤትክርስትያን ተስታውሶ የሚውለውን ዓለም አቀፍ የግኑኝነቶች ቀን በመጥቀስም በተለይ ወጣቶች የዘመኑ ሥልጣኔ ውጤት የሆነውን የግኑኝነት ጥበብ ጓደኝነትን ኅብርትን ምሕረትንና የሰላም ውይይትና ባህልን በሚያጎልብቱ አዎንታውያን ግቦች ላይ ለመድረስ እንዲጠቀሙበት አደራ ብለዋል።

በጉባኤ አስተምህሮው መጨረሻም በሥርዓቱ ላይ ለተሳተፉት ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታና ሐዋርያዊ ቡራኬ አቅርበው በሰላም ወደየመጡበት አሰናበቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.