2009-05-20 15:27:48

የሞምባሳ ሊቀ ጳጳሳት መልእክት


RealAudioMP3 በኬኒያ የሞምባሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቦኒፋቸ ለለ “የአገሪቱ መንግሥት የአገሪቱ ሕዝብ የተደቀነበት አደገኛው ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መፍትሔ እንዲገኝ ለማድረግ መከባበር እንዲሁም ሚዛናዊና ትክክለኛ ወይይት በማስቀደም ብቻ ነው የሚያስፈልገው” በማለት በቅርቡ አገሪቱን በመምራት ላይ ባለው በቅይጡ የፖለቲካ ሠልፍ የተመለመለው መንግሥት እያጋጠመው ያለው አለ መግባባት እና እየከፋ በመሄድ ላይ ያለው ችግር በመጥቀስ ባስተላለፉት መልእክት ማብራራታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

የኬኒያው የብሔራዊው አንድነት መንግሥት ያጋጠመው ውጥረት “በርእሰ ብሔር ኪባኪና በጠቅላይ ሚኒስትር ኦዲንጋ መካከል ያለው አለ መግባባት ያነስሳሳው እና በደጋፊዎቻቸው ተንጸባርቆ እየተባባሰ በመሆኑም ማሕበራዊ ውጥረት እያስከተለ ነው፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት ብፁዕ ኣቡነ ለለ “ቤተ ክርስትያን የማኅበርሰብ ህሊና መሆኗንም ጠቅሰው ህዝቡ ለዕርቅ ለመቀራረብ ለመከባበር ይነቃ ዘንድ የማድረግ ኀላፊነት አላት” እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

ካመራሩ አካላት የመነጨ በህዝቡ ላይ እየተጋረጠ ያለው ችግር፣ አገሪቱን በሞላ የሚመለከት ነው፣ ባጠቃላይ ሙስና አድልዎ ፍርደ ገምድል አሠራር የመሳሰሉት በመስፋፋት ላይ ያሉት ዓበይት ማህበራዊና ሰብአዊ ችግሮች ጠንቅ ይወገዱም ዘንድ መንግሥት ቅድሚያ የስምምነት፤ የመግባባት እና በግብረ ገብ ለተካነ ሕይወት አብነት መሆን አለበት” ብለዋል። በመጨረሻም ባስተላለፉት መልእክት፣ “ተከስቶ ያለው ውጥረት ምክንያታዊና ፍትሓዊ ባለው አገባብ ለመቅረፍ ያላሰለሰ ጥረት ያደረግ ዘንድ” አደራ ማለታቸውም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.