2009-05-20 15:27:30

የመካከለኛው እና የምሥራቅ አፍሪካ ክልል አገሮች ውጥረት


RealAudioMP3 በመካከለኛው እና በምሥራቃዊው ያፍሪካ ክልል አገሮች ባሉት ወጥረቶች አማካኝነት የተፈናቀለው ሕዝብ ብዛት 11 ሚሊዮን መሆኑ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ትብብር ጉዳይ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በምሥራቅ አፍርካ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ ለተለያዩ ክብር ሰራዥ ተግባሮች አልሞ የማዘዋወሩ ጸረ ሰብአዊ ድርጊት እየተስፋፋ መሆኑ የካቶሊክ የአፍሪካ ዕድገት መረጋገጥ ልዩ ጥናት የሚያካሂደው ድርጅት ማስታወቁ ቺሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዚህ ጸረ ሰብአዊ ድርጊት መንስኤ ድኽነት ሥራ አጥነት መሆኑ የጠቀሰው የድርጅቱ መገልጫ፣ ብዙ የዚሁ ክልል ነዋሪው ሕዝብ በኤውሮጳ ላመንዝራነት ንግድ ማገልገያ እንዲሆኑ ተደርገው ለዓቢይ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙና ብዙዎችም ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በጉልበት ሥራ ተቀጥርው እዲሠሩ ተገደው፣ ለተለያዩ ኢሰብአዊ ተግባሮች ተጋልጠው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችለዋል። ለዚህ ኢሰብአዊ ተግባር የተጋለጡት ዜጎች በአገሮቻቸው ጭምር ከዚህ አደጋ የሚገላግላቸውና የወንጀል መቆጣጠሪያ ሕግ ባለ መኖሩ ጭምር ለተለያዩ ኢሰብአዊ አደጋዎች እንዲጋለጡ ምክንያት መሆኑ የድርጅቱ መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.