2009-05-20 15:26:44

እሥራኤልና ዓረብ አገሮች


የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥት በእሥራኤልና በአረብ አገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን አበክሮ እንደሚሠራ፣ የእሥራኤል ዕለታዊ ጋዜጦች ሲጠቁሙ፣ ነገር ግን በቅርቡ በርእሰ ብኄር ባራክ ኦባማና በጠቅላይ ሚኒ. በኒያሚን ናታንያሁ መካከል ተካሂዶ በነበረው ግኑኝነት ሰላም እንዲሰፍን በማድረጉ ሂደት የተለያየ አመለካከት እንዳላቸውም ይናገራሉ።

ሁለት ልዑላን አገሮች የሚለው ያሜሪካ መ RealAudioMP3 ንግሥት የሚያምንበት አመለካከት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒ. ቤኒያሚን ናታንያሁ ይኸንን ሐሳብ ሳይጠቅሱ የፍልስእጤም ራስ ገዝ መስተዳድር የሚለው ቃል መጠቀማቸው ምክንያት፣ በሁለቱ አገሮች መንግሥታት ያለው የሐሳብል ልዩነት ሊንጸባረቅ መቻሉ ይነገራል። በተለይ ደግሞ እሥራኤል በፍልስጥኤም ክልል የምታረማምደው የእሥራኤል መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ማቋረጥ የተባበሩት መንግሥታት ርእሰ ብኄር ኦባማ አንዱ ወደ ሰላም የሚያደርሰው ውሳኔ መሆኑ እንዳመለከቱ ይነገራል። በተካሄደው ግኑኝነት የኢራን የኑክሊያር መርኅ ግብር ርእሰ በማድረግም ጭምር መወያየታቸውም ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.