2009-05-20 15:27:01

ብሩንዲ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 29 ቀን 2003 ዓ.ም. በሰው እጅ የተገደሉት በብሩንዲ የቅድስት መንበር ሐዋርያው ልኡክ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አይዳን ኩርትነይ ጉዳይ እንዲያጣራ የተመለመለው የአገሪቱ ድርገት፣ ባንድ መሣሪያ በታጠቀ የዕለት እንጀራ በመፈለግ ላይ በነበረ ግለ ሰብ እጅ መገደላቸው አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አይዳን ኩርትነይ እ.ኤ.አ. በአይርላንድ የካቲት 5 ቀን 1945 ዓ.ም. ተወልደው፣ እ.ኤ.አ. መጋቢት 9 ቀን 1968 ዓ.ም. የክህነት ማዕርግ ተቀብለው፣ ከመጋቢት 25 ቀን 1980 ዓ.ም. ጀምረውም በቅድስት መንበር በዲፕሎማሲያዊ ዘርፍ ተመድበው በማገልገል በሴነጋል፤ በህንድ፤ በዩጎስላቪያ፤ በኩባ እና በግብጽም ቀጥለውም በኤውሮጳ ህብረት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሆነው አገልግለው፣ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 18 ቀን 2000 ዓ.ም. በብሩንዲ ሓዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ ተመድበው በሰው እጅ እስከ ተገደሉበት ዕለት ማገልገላቸውም ይዘከራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.