2009-05-19 07:16:32

‘‘ቅድስት መሬት የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት ናት’’ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በንግሥተ ሰማያት ጸሎት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ባለፈው እሁድ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከመድገማቸው በፊት በቅርቡ ስለጐበኙት ቅድስት መሬት እንዲሁም የስሪላንካ የወቅቱ ሁኔታን በማስታወስ መልእክት አስተላልፈዋል። RealAudioMP3

ቅዱስነታቸው ባለፈው ሳምንት ወደ ቅድስት መሪተት ስላደረጉት መንፈሳዊ ሓዋርያዊ ጉዞ በሰፊው ነገ ሮብ ሳምንታዊው አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በሚሰጡበት ጊዜ እንደሚገልጹ አሳስበዋል። እግዚአብሔር ይህንን ትልቅ ሓዋርያዊ ጉዞ ለመፈጸም ስላስቻላቸው እንዲሁም ግብኝቱ እንዲሳካ ለተባበሩት የቅድስት መሬት፣ የቤተ ክርስትያንና የመንግሥት ባለሥልጣን የጸጥታ ኃይሎችንና በጸሎት ለሸኙዋቸው ምእመናን አመስግነዋል።

የቅድስት መሬቱ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው እዛ ለሚኖሩት ክርስትያን ግብረ ተልእኮ ለመፈጸም፣ ለክርስትያን አንድነት ሂደት የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት፣ ከአይሁድና እስላም ጋር ለሚደረጉ ውይይቶች ለማበረታታት እና ለሰላም ግንባታ እርዳታ ለመስጠን ያለመ መኖሩን አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.