2009-05-18 14:21:02

የዛምቢያ የእርሻው ልማት አጥጋቢነቱ


ዘንድሮ በዛምቢያ 1.8 ሚሊዮን ቶን የበቀሎ ምርት መሰብሰቡ ተገለጥ። ይህ የሕዝቡ መሠረታዊ የምግብ ፍላጎቱ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። RealAudioMP3 ያገሪቱ የእርሻ ልማት ሚኒስትር ብሪያን ቺቱዎ የሰጡትን መግለጫ የጠቀሰው ሚስና የዜና አገልግሎት፣ ዘንድሮ የተሰበሰበው የበቆሎ ምርት በ 31 በመቶ ከፍ ብሎ መገኘቱና በጠቅላላ የአገሪቱ የእርሻ ልማት ሂደት አመርቂ እየሆነ መምጣቱም አስታውቀዋል።

የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊው የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት መንግሥት ከውጭ አገር የእርሻ ምርቶች የማስግባት ግዴታው በዚህ አመርቂው የግብርናው ልማት አማካኝነትም እየወረደ መምጣቱ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.