2009-05-18 14:16:52

የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች በቅድስት መሬት


በቅድስት መሬት ስላሉት የካቶሊክ ትምህርት ቤቶችና በፍልስጥኤም ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር የሚሰጡት አገልግሎት የፍራንቸስካውያን ማኅበር አባላት፣ በዚህች አገር የቅድስት መንበር ቅዱሳት ሥፍራዎች ጠባቂ፣ ላለው የካቶልክ ትምህርት ቤቶች ተከታታይ ጽ/ቤት ተጠሪ ኣባ ሲሞነ ሄሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ RealAudioMP3 የፍራንቸስካውያን ማኅበር በዚህ ክልል እ.ኤ.አ. በ ከ 1645 ዓ.ም. ጀምረው የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች እንደመሠረቱ አስታውቀዋል። አስታውሰው፣ ትምህርት ቤቶቹ ለሁሉም አለ አድልዎ ክፍት ናቸው፣ በተለይ ደግሞ ድኾችና በጠና ችግር ለተጠቃው የዚሁ ክልል ማኅበረሰብ አሳቢ ትምህርት ቤቶች ናቸው ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ ክልል ባካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት አንዱ ምዕራፍ አይዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የፍልስጥኤም ተፈናቃዮች ጊዚያዊ የመጠለያ ሠፈር ነው። ዩንን በማስመልከት የቅድስት ማርያም ንጹሕ ልብ ፍራንቸስካውያት ማኅበር አባል እናቴ ማሪያ ልዊሳ ከቫትካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ቅዱስ አባታችን ባካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ሰላምና ፍቅር በመቀስቀስ ያስተላለፉት ጥሪ፣ ለሦስቱ የተለያዩ ሃይማኖት ሕዝብ ልብ የሚነቃቃ ይሆን ዘንድ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ። ቅዱስነታቸው በዚሁ መጠለያይ ሰፈር የሚገኙትን በመጎብኘት የነዋሪው ህዝብ ችግር ቀርበው ተመልክተዋል። የቅድስት ቤተ ክርስትስያን እረኛ እዚህ መጥቶ ህዝቡን በማጽናናት ተስፋ ፍቅርና አንድነትን በማበረታታት፣ ክርስትያናዊ ጥሪያችን ሃላፊነታችንም ጭምር አነቃቅተዋል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.