2009-05-18 16:44:41

የኤውሮጳ ወጣቶች በየብፁዓን ተራራ ተገኝተው ጸለዩ፡


በስምንት ሺ የሚገመቱ የተለያዩ የኤውሮጳ ወጣቶች በገሊላ የብፁዓን ተራራ ተገኝተው ጸሎተ ሥርዓት እና አስተንትኖ መፈጸማቸው ተመልክተዋል።

ወጣቶቹ ከመላ ኤውሮጳ የትምህርተ ክርስቶስ እንቅስቃሴ ማኅበረሰቦች የተውጣጡ መሆናቸው ሥርዓተ ጸሎቱ እና አስተንትኖ ያዘጋጁ ባለሥልጣን አስታውቀዋል። RealAudioMP3

ከበርካታ ዓመታት በገሊላ የሚኖሩ ዶን ሪኖ ሮሲ እንዳመለከቱት፡ ወጣቶቹ ገሊላ ላይ ተገኝተው ከፍተኛ እና ማራኪ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አካሄደዋል።

ወጣቶቹ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም በቤተልሔም እና ናዝሬት ተገኝተው መንፈሳዊ መዝሙሮች ጸሎት እና አስተንትኖ በማድረጋቸው የአከባቢውን ሕዝብ መማረካቸውን ዶን ሪኖ ሮሲ ካደረጉት ገለጣ ለመራዳት ተችለዋል።

ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚል መግለጫ አንግበው ኤውሮጳውያን ወጣቶች የቅዱሳን ቦታዎች ወጣቶች መሆናቸው የሚያንጸባርቅ ድርጊት መፈጸማቸው ዶን ሪኖ ሮሲ በተጨማሪ ገልጠዋል።

በዚሁ አከባቢ ያለውን አለመረጋጋት እንዲገታ እና የአከባቢው ሕዝብ በሰላም እንዲኖር ከመጸለያቸው ባሻገር ከስፍራው ወጣቶች ሰላም በተመለከተ ሐሳብ ለሓሳብ መለዋወጣቸውም ተያይዞ ተነግረዋል።

ኤውሮጳ አቀፍ የትምህርተ ክርስቶስ እንቅስቃሴ ስምንት ሺ ወጣቶች መርቶ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተልሔም እና ወደ ገሊላ በመሄድ ለመጸለይ ለማስተንተን የተፈለገበት ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ያደገበት እና ቅዱስ መጽሐፍ የሰበከበት የሞተበት የተነሣበት ከሁሉ የተቀደሰ ቦታ በመሆኑ እንደሆነ ለዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ያዘጋጀ የትምህርተ ክርስቶስ እንቅስቃሴ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.